ውሃ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ውሃ (H2O) በምድር የሚበዛ ፈሳሽ ነው።ውሀ በባህሪው ሽታ.፣ ጣዕም እና ቀለም የለውም።ሕይወት ላላቸው ከሚያስፈልጉ ንጥረነገሮች መካከል አንዱ እና ዋነኛው ሲሆን የሁለት የሀይድሮጅን እና የአንድ ኦክስጂን አጸገብሮት ውሀን ያስገኛል[1]።
ውሀ የመሬትን ሰፊ ክፍል የሚሸፍን ሲሆን ወደ መጠኑም የአለምን 71% ገደማ ነው[2]። በአለም ላይ ከሚገኙ ፈሳሽ ነገሮች ሁሉ ብዙ ነገሮችን ማሟሟት ስለሚችል አለም አቀፍ አሟሚ (Universal Solvent)[3] በመባል ይታወቃል።