ክብደት

From Wikipedia, the free encyclopedia

ክብደት በአንድ ቁስ ላይ የመሬት ስበት የሚያሳርፍበት የጉልበት መጠን ማለት ነው። መሬት ላይ የአንድ ነገር ክብደት ከነገሩ ግዝፈት በንዲህ መልኩ ይለካል፦

W = mg,
  • W ክብደት ነው
  • m የነገሩ ግዝፈት ነው
  • g= 9.8 m/s^2 ሲሆን በመሬት ስበት ምክንያት የሚፈጠረው የቁሶች ፍጥንጥነት ነው;

በርግጥ ቁሶች በመሬት ብቻ ሳይሆን የሚሳቡት በሌሎችም ቁሶች ይሳባሉ። ይህ ክስተት ግስበት ይሰኛል። ለምሳሌ በጨረቃ ወይም ፀሐይ ወይም ማርስ። ባጠቃላይ መልኩ ቁሶች በግስበት ሜዳ ውስጥ ሲገኙ የሚያርፍባቸው የስበት ጉልበት ክብደት ተብሎ ይታወቃል።

የግስበት መጠን ከአንድ ቁስ መካከለኛ ቦታ እየራቅን በሄድን ቁጥር በርቀቱ ስኩየር መጠን ግስበቱ እየደበዘዘ ይሄዳል። በዚህ ምክንያት የግስበቱ ሜዳ ደከመ እንላለን። የመሬትም ስበት ከባህር ወለል ተነስተን ወደ ተራራማው የምድር ክፍል እየወጣን ስንሄድ ግስበቷ እየደበዘዘ ይሄዳል። ስለዚህም የአንድ ቁስ ክብደት በተራራ ላይ ሲቀንስ በባህር ወለል ላይ ይጨምራል። ይህ ጸባይ ከግዝፈት ጋር ይለያያል። የአንድ ነገር ግዝፈት የትም ቦታ አንድ አይነት ነው።

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.