ካዛሉ ወይም ካዛላአካድኛ የጥንታዊ ከተማ ስም ነበር።

በንጉሡ ካሽቱቢላ ሥር፣ ካዛላ በአካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን ላይ ያመጽ ነበር። ሳርጎን ግን «ወደ ካዛሉ ገሥግሦ ካዛሉ የፍርስራሽ ቁልል አደረገው፣ የወፍ መሥፈሪያ ቦታ ስንኳ አልቀረም።»

ላጋሽ ንጉሥ ጉዴአ ዘመን በተቀረጸው ጽላት መሠረት፣ ካዛሉ ከመስጴጦምያ ወደ ምዕራብ በማርቱ ግዛት ይገኝ ነበር። የአሁን ሊቃውንት እንደሚያምኑ ከባቢሎን 15 ኪ/ሜ. ርቀት በኤፍራጥስ ምዕራብ ዳርቻ አካባቢ ነበር። ለአጭር ጊዜ በአሞራውያን ዘመን ካዛሉ ከጎረቤቶቹ አንዳንድ አሸንፎ ይገዛ ነበር፣ ከነዚህም ውስጥ ባቢሎን በካዛሉ ተገዛ። ባቢሎን መጀመርያ ነጻነት ያገኘው (1807 ዓክልበ.) ከካዛሉ ነበር።

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.