የኩሽ መንግሥት
From Wikipedia, the free encyclopedia
የኩሽ መንግሥት በላይኛ አባይ ወንዝ በጥንት የተመሠረተ አፍሪካዊ መንግሥት ነበረ።
በኢትዮጵያ ታሪክ ጸሓፊዎች ዘንድ የኩሽ መንግሥት በካምና በልጁ ኩሽ ተመሠረተ። ይህ የኩሽ ወይም የኩሳ ሥርወ መንግሥት ግዛት እስከ ደጋ ድረስ ሲዘረጋ አንዳንድ ጎሣ ከውጭ አገር በተለይ ከከነዓን በዚያ ይሠፈር ነበር።
«ኩሽ» የሚለው ስም መጀመርያ በግብጽ መዝገቦች የታየው በ2 መንቱሆተፕ ዘመን ነው። ያው ፈርዖን በ2092 እና 2090 ዓክልበ. ግድም ከ2ኛው ፏፏቴ ወደ ደቡብ በኩሽ ላይ ዘመተ።
ከ16ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. እስከ 11ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ድረስ ኩሽ በዛሬው ሱዳን ለግብጽ አዲስ መንግሥት ተገዥ ነበር። ከዚያ እንደገና ነጻ ሆነ፣ በ8ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. የኩሽ ነገሥታት ደግሞ በግብጽ የ25ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖኖች ሆኑ፤ እስከ ሶርያም ድረስ አገሩን አቀኑ።