ዕድል ጥናት
From Wikipedia, the free encyclopedia
[1]የዕድል ጥናት የአንድን ወይም ከዚያ በላይ ኩነት እውን የመሆን ዕድል (መጠነ አዝማሚያ) የሚያጠና የሒሳብ ክፍል ነው። ለምሳሌ ሳንቲም በአየር ላይ ተወርውሮ መሬት ላይ ሲያርፍ "ፊት" ወይም "ግልባጭ" የመሆን ኩነት ያጋጥማል። ፊት የመሆን አዝማሚያውን የምንለካው በዕድል ጥናት ሲሆን በአጠቃላይ ሁለት ኩነቶች ስላሉ፣ ከሁለቱ አንዱ የመሆን ዕድሉ 1/2ኛ ወይም 0.5 ነው እንላለን።
በአጠቃላይ መልኩ "እድል ጥናት" ማለት የአንድን ወይም ከዚያ በላይ ኩነት የመሆን አዝማሚያ እምነት ወይም እውቀት የምንገልጽበት መንገድ ነው። በአሁኑ ዘመን ዕድል ጥናት ሁለት አይነት አንድምታ ይይዛል፤
- ፩ - ከድግግሞሽ አጥኒወች አንጻር፡ ዕድል ማለት አንድ ዘፈቀደ ሙከራ ተካሂዶ፣ ያ ሙከራ ሲደጋገም የአንድ ክስተት (ኩነት) በኒህ ሙከራወች ውስጥ የመደጋገም መጠን ማለት ነው። በድግግሞሽ አጥኒወች ዘንድ፣ እድል ማለት፣ ከብዙ ሙከራወች በኋላ አንድ ኩነት የሚያሳያው አንጻራዊ ድግግሞሽ መጠን ማለት ነው። ለምሳሌ ሳንቲምን ወደ ላይ በማጉናት ሙከራ ብናደርግና ይህን ሙከራ 1 ቢሊየን ጊዜ ብንደጋግመው፣ "ፊት" የማግኘቱ ድግግሞሽ ስንት ጊዜ ነው? በተመክሮ ይህ ቁጥር 500 ሚሊየን ጊዜ ቢሆን የዚህ ክስትተት አንጻራዊ መጠን እንግዲህ 500 ሚሊየን ሲካፈል ለ 1 ቢሊየን - ምለት 0.5 ነው ማለት ነው።
- ፪- ከባዬዢያኖች አንጻር፣ ዕድል ማለት የአንድ ግለሰብ በአንድ ዓረፍተ ነገር ላይ ያለውን እምነት መጠን የሚለካ ነው። ወይም በሌላ አባባል፣ ማስረጃ በቀረበለት ዓረፍተ ነገር ላይ አንድ ግለሰብ ያለው ቀልበኛ ዕምነት መጠን ማለት ነው።