From Wikipedia, the free encyclopedia
እስኩቴስ (ግሪክ፦ Σκυθία /ስኩጢያ/) በአውሮጳና በእስያ የተገኘ ጥንታዊ አገር ነበረ።
የእስኩቴስ ሰዎች (ግሪክ፦ Σκύθες /ስኩጠስ/) በታሪክ መዝገቦች መጀመርያ የሚታዩ በ700ዎቹ ዓክልበ. ሲሆን በአሦር ሰነዶች ውስጥ አሽኩዝ ተብለው ነው። ዳሩ ግን በኋላ ዘመን በጻፉት መምህሮች አፈ ታሪክ ዘንድ ከማየ አይኅ ቀጥሎ ከሁሉ አስቀድሞ የኖረ አገር ነበሩ። በቋንቋቸው በእስኩቴስኛ ለራሳቸው የነበራቸው ስያሜ ስኩዳ እንደ ነበር ይመስላል። በምሥራቅ አገሮች ግን ሳካዎች (ፋርስኛ፦ ሳካ፣ ቻይንኛ፦ 塞 /ሳይ/) ተባሉ። ግዛታቸው እጅግ ሰፊ ሆኖ ለረጅም ዘመን ከዳኑብ ወንዝ በአውሮጳ እስከ ሞንጎልያ፣ ቻይናና ሕንድ ጠረፍ ድረስ ይስፋፋ ነበር።
በአውሮጳም ሆነ በእስያ ከአይርላንድ እስከ ካምቦድያ ድረስ በጣም ብዙ ብሔሮች ከእስኩቴሳውያን እንደተወለዱ የሚል ልማድ አላቸው።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.