ኤአናቱም ከ2254 እስከ 2195 ዓክልበ. ድረስ ግድም የሱመር ከተማ ላጋሽ ንጉሥ ነበረ። አንድ ጽሑፍ እንደሚገልጸው ስሙ በሱመርኛ «ኤአናቱም» ሲሆን የቲድኑ (ሶርያ) ስያሜው «ሉማ» ነበረ። በርሱ መሪነት ላጋሽ ሰፊ ግዛት ይይዝ ነበር።
ኤአናቱም የአኩርጋል ልጅና ተከታይ ሲሆን የላጋሽ ንጉሥ ከሆነ በኋላ ሌሎቹን ከተሞች ለመያዝ ጀመረ። ኪሽን (ምናልባት ከንጉሡ ካልቡም) ጨመረ። በሐማዚ ንጉሥ ሀዳኒሽ ዘመን ደግሞ ትልቅ እንደ ነበር ይቻላል፤ በኋላ ዘመን በኒፑር መቅደስ «ሀዳኒሽና ሉማ» የተባሉ የአናብስት ሀውልቶች ነበሩ። በኡሩክ ንጉሥ ኤንሻኩሻና ዘመን ኤአናቱም በተለይ አሸናፊ ሆነ፤ የአክሻክ ንጉሥ ዙዙን ድል አደረገ፤ ከዚያ በኋላ ላርሳ፣ ኡማና ዑር ከኤንሻኩሻና ያዘ። ከዚህ በላይ ኤአናቱም መንግሥቱን ወደ ስሜን እስከ ሹቡርና እስከ ማሪ ድረስ አስፋፋ፤ ኤላምንም ወረረ። በመጨረሻ በ2195 ዓክልበ. ግድም ኡሩክና ኒፑር ወድቀው ኤንሻኩሻናን ገለበጠው። ትንሽ ከዚህ በኋላ ግን ኤአናቱም ሞቶ ግዛቱ እንደገና በየከተማው ተከፋፈለ። ስለዚህ የኤንሻኩሻና ልጅ ሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ የሱመር ላዐላይነቱን ከኡሩክና ኒፑር ያዘ። የኤአናቱም ወንድም ኤናናቱም የላጋሽ አለቃ ወይም ከንቲባ ሆነ።
ኤአናቱም በተለይ የሚታወቅበት «የአሞራዎች ጽላት» ስለሚባለው ቅርስ ነው። ይህ ትርዒት የኤአናቱም ድል በኡማ ንጉስ ኤናካሌ ላይ ለማስታወስ ተቀረጸ።
ቀዳሚው አኩርጋል |
የላጋሽ ገዥ 2254-2195 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ኤናናቱም |
ቀዳሚው የኡሩክ ንጉሥ ኤንሻኩሻና |
የሱመር አለቃ 2195 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ የኡሩክ ንጉሥ ሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ |
Wikiwand in your browser!
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.