ኤብላ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ኤብላ የሶርያ ጥንታዊ ከተማ ነበር። ዛሬው ሥፍራው በአረብኛ ተል ማርዲኽ ተብሎ የኤብላ ጽላቶች የተገኙበት ፍርስራሽ ነው።
ከአካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን አስቀድሞ በሆነው ዘመን ኤብላ ሰፊ መንግሥት በሶርያ ዙሪያ እንደ ነበረው ይታወቃል። የጽላቶች ቤተ መዝገብ ሕንጻ የተቃጠለበት ጊዜ የሚከራከር ነው። ሦስት ዋና አስተያየቶች አሉ፤ 1) ከሳርጎን በፊት በኤብላ ተፎካካሪ በማሪ፤ 2) በሳርጎን እራሱ፤ ወይም 3) በሳርጎን ልጅ ልጅ በናራም-ሲን። አሁን በሳርጎን ዘመን በ2074 ዓክልበ ግድም እንደ ጠፋ ቢመስልም በሳርጎን ወይም በማሪ ሰዎች እጅ መጥፋቱን እርግጠኛ አይደለም።