ኤስፔራንቶ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ኤስፔራንቶ (Esperanto) ከሁሉም አለማቀፋዊ ሠው ሰራሽ ቋነቋዎች እጅጉን የተስፋፋ ቋንቋ ነው። በ1859 እ.ኤ.አ. በዛሬይቷ ፖሎኝ የተወለደውና በሞያው የአይን ሀኪም የሆነው ሉድዊክ ሌይዛር ዛመንሆፍ በ1887 እ.ኤ.አ. ቋንቋውን ለህዝብ አሳወቀ። አላማው ኤስፔራንቶን በቀላሉ ሊማሩት የሚቻል፣ የጋራ የሆነና ለአለማቀፋዊ መግባባት የሚረዳ ግን ያሉትን ቋንቋዎች የማይተካ ቋንቋ ማድረግ ነበር። ኤስፔራንቶ ከ1,600,000 በላይ ተናጋሪዎች ቢኖሩትም የቋንቋው ደጋፊ ያልሆኑ እንግሊዝኛን ከመስፋፋቱ አንፃር ለአለማቀፋዊ ቋንቋነት በተሻለ ይመርጡታል።