ኢትዮጵያ
በምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር / From Wikipedia, the free encyclopedia
ኢትዮጵያ ወይም በይፋ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.) በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነቷን ጠብቃ የኖረች ብቸኛ ሀገር ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን ፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ናት።
ይህ መጣጥፍ ምንም ዓይነት የዋቢ ምንጮች አያካትትም። እባክዎን ተገቢ ምንጮን በመጥቀስ ያሻሽሉት። (፬ ነሐሴ ፳፻፮) |
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: ወደፊት ገስግሺ፣ውድ እናት ኢትዮጵያ |
||||||
ኢትዮጵያ በቀይ ቀለም
|
||||||
ዋና ከተማ | አዲስ አበባ | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | አማርኛ ሌሎች ቋንቋዎች ክልላዊ ዕውቅና አላቸው | |||||
መንግሥት {{{ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር |
ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ ዶ/ር አብይ አህመድ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
1,104,300 (26ኛ) 0.7 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ፳፻ ዓ.ም. ግምት የ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. ቆጠራ |
93,578,567 (13ኛ) 96,787,564 |
|||||
ገንዘብ | ብር (ETB) | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +3 | |||||
የስልክ መግቢያ | 251 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .et |
አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ-ዓመት የሚያንስ ሲሆን ፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በንጉሠ-ነገሥታት እና ንግሥተ-ነግሥታት የተመራች ሀገር ናት። የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት የአመጣጡን ዘር እስከ አስረኛው ዓመተ-ዓለም ድረስ ይቆጥራል። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የኖረባት ቦታ እንደሆነች ብዙ የሳይንሳዊ መረጃ ተግኝቷል። በበርሊን ጉባኤ በኩል የአውሮፓ ሀያላት ሀገሮች አፍሪካን ሲከፋፍሏት፣ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃለች። የሊግ ኦፍ ኔሽንስ (League of Nations) አባል ከነበሩት ሶስት የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነበረች። ከአጭር የኢጣልያ ወረራ ጊዜ በኋላም ከየተባበሩት መንግሥታት መሥራቾች አንዷ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን ሲያገኙ፣ ሰንደቅ-አላማቸውን በኢትዮጵያ ቀለሞች ማለትም በአረንጓዴ ፣ ቢጫ እና ቀይ ላይ ነው የመሠረቱት። አዲስ አበባ ደግሞ ለየተለያዩ በአፍሪካ ላይ ላተኮሩ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ ሆነች።
የዛሬዋ ኢትዮጵያ የትልቅ የግዛት ለውጥ ውጤት ናት። ከሰሜን ግዛቱዋ በጣም የተቀነሰ ሲሆን በደቡብ በኩል ደግሞ ተስፋፍቷል። በ ፲፱፻፷፯ (1967) ዓ.ም.፣ ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከሥልጣን ሲወርዱ፣ የእርስ በርስ ጦርነት በሀገሩ ተባባሰ። ከዚህ ጊዜ በኋላ ኢትዮጵያ በተለያዩ የመንግሥት አይነቶች ተዳድራለች። ዛሬ አዲስ አበባ የአፍሪካ ሕብረት (African Union) እና የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለአፍሪካ መቀመጫ ናት። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ከአፍሪካ ኃያል ሠራዊቶች አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪቃ የእራሷ ጥንታዊ ፊደል ያላት ሀገርም ናት።
ኢትዮጵያ ተፈጥሮ ያደላት ሀገር ናት። ከአፍሪካ ትላልቅ ተራራዎች እንዲሁም ከዓለም ከባህር ጠለል በታች በጣም ጥልቅ ከሆኑ ቦታዎች አንዳንዶቹ ይገኙባታል። ሶፍ ዑመር ከአፍሪካ ዋሻዎች ትልቁ ሲሆን ፣ ዳሎል ከዓለም በጣም ሙቅ ቦታዎች አንዱ ነው። ወደ ሰማንኒያ የሚቆጠሩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ዛሬ በኢትዮጵያ ይገኛሉ። ከእነዚህም ኦሮሞና አምሀራ በብዛት ትልቆቹ ናቸው። ኢትዮጵያ በኣክሱም ሓውልት፣ ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍለው በተሰሩ ቤተ-ክርስትያኖቹዋ እና በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ አትሌቶቹዋ ትታወቃለች። የቡና ፍሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በኢትዮጵያ ሲሆን ሀገሪቱዋ በቡናና ማር አምራችነት በአፍሪካ ቅድሚያ ይዛለች።
ኢትዮጵያ ከዓለም ሶስቱ ትላልቅ የአብርሃም ሀይማኖቶች ጋር ታሪካዊ ግንኙነት አላት። ክርስትናን በአራተኛው ምዕተ-ዓመት ተቀብላለች። ከሕዝቡ አንድ ሁለተኛው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ነው። የመጀመሪያው የእስላም ሂጅራ ወደ ኢትዮጵያ ነው የተከናወነው። ነጋሽ በአፍሪካ የመጀመሪያው የእስላም መቀመጫ ናት። እስከ ፲፱፻፸ ዎቹ ድረስ ብዙ ቤተ-እስራኤሎች በኢትዮጵያ ይኖሩ ነበር። የራስ ተፈሪ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን በትልቅ ክብር ነው የሚያያት።
ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ድህነት በኢትዮጵያ በጣም ተስፋፍቶ ነበር። ሰማኒያ አምስት ከመቶ በላይ የሚሆነው የአባይ ወንዝ ውሀ ከሀገሩ የሚመጣ ቢሆንም በ ፲፱፻፸ ዎቹ በተከሰቱ ድርቆች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል። ያንን ካሳለፈች በኋላ ሀገሪቱዋ አዲስ መንገድ በመፈለግ ላይ ትገኛለች።
“ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል ትርጉሙንና አመጣጡን ለመመርመር በ፲፱፻፹፩ (1987 እ.ኤ.አ.) በወጣው ሰምና ወርቅ በተባለው የምርምር መጽሔት ፪ኛ ዓመት፣ ቁጥር ፬ አጥር ያለ ጽሑፍ አቅርበን፣ አንዳንድ ምሁራን፤ “ኢትዮጵያ ማለት ከግሪክ ቋንቋ የመጣ ቃል፣ ‘ፊቱ በፀሓይ የተቃጠለ፣ የተጠበሰ፣ ያረረ’ ማለት ነው ...” የሚሉት ትክክል እንዳልሆነ ለማሳየት፤ ናይጀርያ የሚባል አገርና፣ (Nigeria) ኒጀር (Niger) የሚባሉ አገርና ወንዝ በአፍሪካ እንዳሉ ጠቅሰን፣ ኔግራ፣ ኔግሮ፣ ኒገር፣ ኔግሪትዩድ (Negra, Negro, Nigger, Negritude) ለሚሏቸው ቃላት ወደ ላቲን/እንግሊዝኛ ቋንቋ ለመግባት ምክንያት ሆኑ እንጂ፣ ከላቲን ቋንቋ ተወስዶ ለአፍሪካ አገሮችና ወንዝ የተሰጠ ስም አይደለም በማለት፣ ኢትዮጵያ የሚለውም ቃል እንዲሁ ጥንታዊ ምንጩ ከግሪክ ሳይሆን ከአገራችን የወጣ ቃል መሆኑን ለመግለጽ ሞክረን ነበር።
አንድ-አንድ ቃላትን ስንመረምር በውስጣቸው የተደበቅ ምስጢር እናገኛለን። የተደበቀውን ምስጠር ለማግኘት ጥልቅ የታሪክና የቃላት ምርምርና ጥናት (Philology / Etimology) ማድረግ ያስፈልጋል። በብዙ ምርምርና ጥናትም ምስጢሩ የሚገለጥበት ጊዜ አለ። ለምሳሌ በግዕዝ፣ በትግርኛና፣ አማርኛ ‘አነ’፣ ‘እኔ’ የሚሉ ቃላት ስናገኝ፣ በላቲን/በእንግሊዝኛ ደግሞ ‘አይ’ (I - እንግሊዝኛ)፣ ‘ኢዮ’ (Io -ጣልያንኛ) አሏቸው። በግዕዝ፣ ትግርኛና፣ አማርኛ ‘ዓይን’ ‘ዓይኒ’ ለሚሉ ቃላት ደግሞ፣ በእንግሊዝኛ አይ (eye) እናገኛለን። በአማርኛና ትግርኛ፤ ‘ያለቀለት ጉዳይ’ ለማለት ‘ሙት፣ የሞተ ነገር’፣ ስንል በእንግሊዝኛ ‘ሙት ኢሹ’ (moot issue) ይላሉ። በግዕዝና፣ ትግርኛ፣ ‘መርዓ’ ስንል፣ በእንግሊዝኛ (marriage) ‘መረጅ’ ይላሉ። ፈርኦን (Pharaoh) ከሚባል ጥንታዊ የግብፅ ንጉሥም ወደ ግዕዝ፣ ትግርኛና አማርኛ፣ እንዲሁም ወደ እንግሊዝኛ ቃላት፤ ‘ፈሪሃ’ ‘ፍርሓት’ ‘fear’ (ፊር) ለሚሏቸው ቃላት ምንጭ የሆነ ይመስላል። ንጉሡ ታላቅና የሚፈራ የነበረ ነው የሚመስል። እነዚህን ለምሳሌ አቀረብን እንጂ እንደዚህ ብዙ የቃላት መቀራረብ እናገኛለን። “ማን ከማን ወሰደ? ታሪካዊ አመጣጡና አወራረዱስ እንዴት ነው?” የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ነው የቃላት ጥናትና ምርምር የሚያስፈልግ።
አንድ-አንድ ቃላትም ከቋንቋችን ፈልቀው ይወጡና ዓለምን ዞረው ተመልሰው ሲመጡ ብርቅ አድርገን እንቀበላቸዋለን። ለምሳሌ በኃይለሥላሴ ዘመን ያኔ ልዕልት ፀሓይ ሲባል ከነበረው ሆስፒታል ጎን አዲስ የሕንፃ ኮሌጅ ተከፍቶ፣ ‘የመሃንድስ ኮሌጅ’ በመባል ይታወቅ ነበር። መሃንድስ ማለት ምን ማለት ነው? መሃንድስ ማለት መሃናስ/መሃንዳሰ ከሚል የዓረብኛ ቃል የመጣ ሲሆን፣ እርሱ ደግሞ ሃነፀ፣ ይሃንፅ፣ ማነፅ፣ ማሕፀን (ሕፃን የሚታነፅበት ቦታ) ... ወዘተ ከሚሉ የግዕዝ፣ የትግርኛና፣ የአማርኛም ቃላት ይዛመዳል። እንግዲያውስ ማነፅ ከሚለው ቃል መሃንዳስ ሆኖ ተጣመመና፣ ከዚያም መሃንድስ ተብሎ፣ ዞሮ ተመልሶ ብርቅ ቃል ሆኖብን ለሕንፃ ኮሌጀ መጠሪያ ሆነ። አሁንም ቢሆን ኢንጂኔር ለማለት መሃንድስ ሲባል እንሰማለን።
ሌላም ቃል ፋጡማ/ፋጢማ የሚል ስም ስንመለከት፣ ከነብዩ ሙሓመድ ሴት ልጆች ለአንዷ የተሰጠ መጠሪያ ነበረ። በዓረብኛ አባባል ግን ጠ/ጸ የሚለው ሳይሆን ተ የሚለው ፊዴል ድምፅ ነው። ይህም ማለት፣ ቃሉ “ፈቲማ” ብለው ሲሉ፣ ትርጉሙም፡ ፍጽምት፣ (Perfect) ማለት ነው። ስለዚህ ፈቲማ ማለት፣ ፈጺማ (ትግረኛ) ፈጸመች (አማርኛ) ማለት ነው።
ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ሰምና ወርቅ በተባለው የምርምር መጽሔት (1987 እ.ኤ.አ.) ያቀረብነው፣ “ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ትርጉሙ ምን ማለት ነው? ኢትዮጲስ የሚባለው ንጉሥስ ለምን ይህ ስም ተሰጠው ... ብለን በጠየቅንበት ጊዜ አጥጋቢ መልስ ባለማግኘታችን ቋንቋ ለሚመረምሩ (linguists) እንዲያተኩሩበት በዚሁ እንተወዋለን” በማለት ምርምሩን ደመደምነው።በዚህም ይህን መልስ አግኝተናል ኢትዮጲስ በመጽሐፈ አክሱም ዘንድ ኑቢያን የመሠረተው የካም ልጅ ኩሽ ልጅ ነበር። በዚህ መሠረት በኢትዮጵያ የሚኖሩት ኩሺቲክ ብሔሮች አባት በመሆኑ አገሩ 'ኢትዮጵያ' መባሉ እንደሚገባው ይታመናል።
በተክለ ጻድቅ መኩሪያ የተጻፈው “የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ኑብያ፣ (ናፓታ-መርዌ)” በተባለው መጽሐፍ በገጽ19-22 የካም ወገን የሆኑ 22 ነገሥታ
- ን ስምጠቅሶ፣ 55 ዓመት ከገዛው ከአክናሁስ ወይም ሳባ ፪ኛ (1985-1930 BC) ከክርስቶስ ልደት በፊት አንስቶ የ29 ነገሥታትን ስም አስቅምጦ፤ “... ራማ የተባለ የህንድ ንጉሥ ወደ ኢትዮጵያ ዘምቶ ማሸነፉንና ሕዝቡን እንደ ባርያ ...” ይገዛው እንደ ጀመረ ያትታል። ከዚያ ግን ሦስት የዮቅጣን ልጆች ተባብረው ተነስተው እሸነፉት፥ ገድለውም፣ አግዓዝያን (ነፃ አውጭዎች) ተብለው መንግሥቱን እንደ ያዙ ገልጾ፣ ከዚያ ቀጥለው የነገሡትን የ52 የኢትዮጵያ ነገሥታት ስም ይዘረዝራል። ከፊተኞቹ 29 ነገሥታትም የመጀመሪያዎቹ 10 ነገሥታት የሚከተሉት ናቸው:-
The meaning of the name Ethiopia
ከዚህም ዓምድ እንደሚታየው ኢትዮጲስ ፩ኛ ከ1856-1800 ከክርስቶስ ልደት በፊት፣ ለ56 ዓመት መንገሡ፣ ኢትዮጲስ ፪ኛው ደግሞ ከ1730-1700 ከክርስቶስ ልደት በፊት፣ ለ30 ዓመት ያህል መንገሡ በታሪክ ተጽፏል። ይህንን ያላነበቡ ምሁራኖቻችን ግን ኢትዮጵያ ማለት ከግሪክ ቋንቋ የመጣ ቃል፤ ‘ፊቱ በፀሓይ የተቃጠለ፣ የተጠበሰ፣ ያረረ ማለት ነው’ ይሉናል።
ታላቁ የግሪክ ተራኪና ባለ ቅኔ፣ ሆመር የኖረው 800 - 700 ከክርስቶስ ልደት በፊት ሲሆን፣ የግሪክ ስልጣኔ ዘመን ወይም የሄሌኒስቲክ ኤጅ (Hellenistic Age) ተብሎ የሚታወቀውም ከታላቁ እስክንድር ዘመን አንስቶ፣ ማለትም 300-30 ከክርስቶስ ልደት በፊት ድረስ ያለው ጊዜ ነው። ይህ ማለት ኢትዮጲስ ፩ኛ ከባለቅኔው ከሆመር በፊት አንድ ሺሕ ዓመት ቀድሞ የነገሠ ንጉሥ ነው።
እንግዲያውስ ምሁራኖቻችን ኢትዮጵያ ማለት ከግሪክ ቋንቋ የመጣ፤ ‘ፊቱ በፀሓይ የተቃጠለ፣ የተጠበሰ፣ ያረረ ማለት ነው’ ሲሉን፣ ሊመልሷችው የማይችሉ ሁለት ጥያቄዎች አሉን፣
1 - የጥንት የአገራችን ነገሥታት የግሪክን ቋንቋ ከሆመር መወለድ በፊት አንድ ሺሕ ዓመት አስቀድመው እንደምን ዐወቁት? ዘመኑ አቴናውያንና ስፓርታውያን የእርስ-በርስ ጦርነት (peloponnesian war 431-404 ከክርስቶስ ልደት በፊት) አንድ ሺሕ አራት መቶ ዓመት በፊት ነው። የግሪክ ቋንቋም በአካባቢው ከነበሩ መቄዶንያ፣ ማግያር፣ አናጦልያ ... ወዘተ ከመሳሰሉት ቋንቋዎች በምኑም ተለይቶ የሚታወቅ፣ ወይም የገነነ ልሳን አልነበረም። ስለዚህ እንዴት ተብሎ ይህንን ስም የአገራችን ነገሥታት ከግሪክ ቋንቋ ወሰዱት ማለት ይቻላል?
2 - ቋንቋውን ቢያውቁና ቃሉን ከግሪክ ወሰዱት ብንልም፣ እንዴት የአገራችን ነገሥታት ራሳቸውን፤ “ፊታችን በፀሓይ ያረረ፣ የተጠበሰ፣ የተቃጠለ ነውና ራሳችንን ኢትዮጲስ፤ ‘ፊታቸው በፀሓይ ያረረ፣ የተጠበሰ፣ የተቃጠለ’ ብለን እንጥራ ...” ብለው የራሳቸውን የንግሥ ስም አወጡ? ይህ ዓይነቱ አባባል ይታመናል? ፈጽሞ የማይመስል ወሬ ነው።
ምሁራኖቻችን እነዚህን ሁለት ጥያቄዎች ሲጠየቁ፣ “አፋፍ-ላፋፍ ስትሄድ አግኝቸ ሚዳቋ፣ በጅራቷ ብይዛት ዓይኗ ፍጥጥ አለ ...” እንደሚሉት ዓይናቸውን ከማፍጠጠና ከመቅበዝበዝ በቀር ሌላ የሚያድርጉት ሆነ የሚሰጡት ምንም መልስ የላቸውም።
በግሪክ ቋንቋ Αιθιοπία (አይትዮፕያ) ማለት ፊቱ በፀሓይ የተቃጠለ፣ የተጠበሰ፣ ያረረ ማለት ለመሆኑ አያጠያይቅም። ጥያቄው፤ የትኛው ቃል ከየትኛው መጣ? ነው። ግሪኮች የአገራችን ጥቁር ሰው አይተው ነው ቃሉን ወደ ቋንቋቸው ያስገቡት፣ ወይስ የአገራችን ነገሥታት ናቸው ስማቸውን ከግሪክ ቋንቋ ወስደው ለራሳቸው መጠሪያ ያደረጉት? ጥያቄው ይህ ነው!
የዚህ ዓይነቱ የተዛባ አስተሳሰብ የተላበሰ አንድ የሃይማኖት መሪ፤ “... ድንቅና ተአምር የሆነ የእግዚአብሔር ጥበብ የሚገርም ነገር አለ፣ ዓይናችን፣ አፍንጫችንና፣ ጆሮአችን እንዴት ብሎ ለመነጽር እንደሚገጥም ሆኖ መፈጠሩ ዕጹብ አይደለም?” እያለ ሰብኳል ይባላል። ይህ ግን የትኛው ቀዳሚ፣ የትኛው ኋለኛ መሆኑን ባለማወቁ ነው። መነጽር ነው ለዓይን፣ ለአፍንጫና ለጆሮ እንዲገጥም ሆኖ የተሠራ እንጂ፣ ፊታችን ለመነጽር እንዲገጥም ሆኖ አልተፈጠረም። ጥልቀት የሌለው ዐውቃለሁ ባይነት ግን ለእንዲህ ዓይነቱ መዘላበድ ያጋልጣል።