አይሳክ ኒውተን
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሰር አይሳክ ኒውተን ከ[[ጃንዩዌሪ] 4 ቀን [[1663 እ.ኤ.አ.] እስከ ማርች 31 ቀን 1727 እ.ኤ.አ. የኖረ እንግሊዛዊ የፊዚክስ፤ የሒሳብ፤ የስነ ክዋክብት፤ የስነ መለኮት፤ የተፈጥሮአዊ ፍልስፍና እና ጥንት የነበረው የአልኬሚ ምሁር ነበረ። ምናልባትም ኒውተን በጣም ከሚታወቅባቸው ነገሮች ውስጥ ሶስቱ የኒውተን ሥነ-እንቅስቃሴ ህጎች ፤ የኒውተን የግስበት ቀመር፤ ካልኩለስ ለተባለውን የሒሳብ ክፍል መጀመር (ይህን ክብር ከጀርመናዊው ምሁር ከጎትፍሪድ ሌብኒትዝ ጋር ይጋሩታል)፤ ስለ ብርሃንና ስለሚይዛቸው ቀለማት ያገኘው ግኝት ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም ኒውተን የእንቅስቃሴ ህጎችን በመጠቀም የፕላኒቶች (ፈለገ ሰማያት) እንቅስቃሴ በነዚሁ ህጎች እንደሚመሩ በማሳየት እና የሌላ ምሁር የጃናንስ ኬፕለር የፕላኒቶች እንቅስቃሴ ህግ ጋር እንደሚጣጣም በማሳየት ፤ በፊት ይታመንበት የነበረውን መሬት የሁሉም ነገሮች ማዕከል ናት የሚባለውን ሐሳብ ትክክል እንዳልሆነ በሳይንሳዊ መንገድ አሳይቷል።