From Wikipedia, the free encyclopedia
ጋኔን (ነጠላ) ወይንም አጋንንት (ብዙ ቁጥር) የእርኩስ መንፈስ አይነት ሲሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ ተመዘው በተስፋፉ ጽሑፎች ላይ የዚህ መንፈስ ታሪክ/አፈ-ታሪክ ተጽፎ ይገኛል። ለምሳሌ ቀኖናዊ ባልሆኑት ስነ ፍጥረት እና ሰይፈ ስላሴ በተባሉ የግዕዝ መጻሕፍት።
አሁንም ብዙው ህብረተሰብ እንዲህ ያስባል። በመጽሐፍ ቅዱስ ስለሚጠቀሱ፣ እስካሁን ድረስ በዓለም ዙሪያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ትምህርት እንዲህ ይመስላል። አጋንንት የሳይንስ እውቀት ባላቸውም ሆነ በሌላቸው ኢትዮጵያውን ዘንድ እጅግ ከፍተኛ ፍርሃቻን የሚፈጥር አስተሳሰብ ነው። ነገር ግን የአጋንንት ታሪክ የሚመነጨው የሳይንስ አስተሳሰብ ባልተስፋፋበትና ስለቫይረስም ሆነ ጀርም በማይታወቅበት ዘመን ሲሆን ዘመናዊው የሳይንስ አስተሳሰብ ከዚህ ይለያል፣ እንደሚከተለው ይላል፦ ዋና ዓላማውም የበሽታዎችን አመጣጥ በሚያሳምን መልኩ ለመረዳት እና ለመተንበይ ነበር። ይሄ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአብዛኛው ያልተማረ ህብረተሰብ የሚሰራበት የነበር ነው። ስለሆነም ሆድ ቁርጠት፣ ጉስምት፣ ብድብድ ወዘተ በአጋንንት ምክንያት የሚመጡ ተደርገው ይታሰቡ ነበር።
እንደ ሰይፈ ስላሴ ታሪክ፣ በሰማይ ቤት 100 የመላዕክት ነገዶች ነበሩ። ከለታት አንድ ቀን እግዚአብሔር በሌለበት፣ ሰባልስዮስ ወይንም ሰይፈ ስላሴ የተሰኘ የመላዕክት አለቃ እኔ ሁሉን ፈጠርኩ አለ። ከ100ዎቹ ነግዶች አንደኛው ወገን ይህን የሰባልስዮስን ቃል አመነ። ይሄው ቡድን ወደ እሳት ተጣለ። ከሳት ከወጣም በኋላ የሰይጣን አገልጋይ ሆነ፡፡ የነገዱ አባላቶችም መጠሪያ ስማቸውም አጋንንት ሆነ።
እንደዚሁ አፈ ታሪክ 99 የመላዕክት ነገዶች ስለቀሩ እግዚአብሔር 100ውን ለመሙላት አዳምን ፈጠረ፡፡ ሆኖም አዳም ከጭቃ ስለተሰራ እና ሰይጣን ደግሞ ከአየር እና ብርሃን ስለተሰራ፣ ሰይጣን ለሰው ልጅ ክብር መስጠት እምቢ አለ፣ ስለዚህም በሁለቱ መካከል የማያቋርጥ ጠብ አለ።
ከላይ እንደተጠቀሰው አብዛኛው በሽታ በአጋንንት ምክንያት የሚመጡ እንደንበር በብዙዎች ይታመን ነበር። ስለሆነም አንድ ግለሰብ በሽታ ሲይዘው እርሱን ለማዳን አንዱ አማራጭ አጋንንት የያዘውን ሰው በዛር መንፈስ በማስያዝ አጋንንቱን ከውስጡ ማስለቀቅ ነበር። የዛር መንፈስ ከአጋንንት ይሻላል ተብሎ ስለሚታመን። ፀበል፣ ቁርባን እና እንዲሁም የእርግፍጋፎ እንጨት (Protea Abyssinica) ለፈውስ ይረዳሉ ተብለው ተጠቃሚነትን ያገኛሉ[1]። ለኤድስ እና ሌሎች የቫይረስ እና ጀርም በሽታዎች በፀበል ፈውስ መፈለግ መሰረቱ ከዚህ የተዛባ ግንዛቤ ይፈልቃል።
በወንጌሎች በተለይም በማርቆስ ወንጌል ዘንድ፣ ኢየሱስ በልዩ ልዩ ደዌ ወይም በሽታ የተሰቃዩትን ሰዎች እየፈወሰ፣ ጋኔን ወይም ርኩስ መንፈስ ካደረበት ሰው ጋኔኑን በቃሉ ያወጣል። (ማቴ. 4፡24፣ 8፡16፣ ማርቆስ 1፡32-34፣ 39፤ ወዘተ.)
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.