አይጥ

From Wikipedia, the free encyclopedia

አይጥ

አይጥኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሁም በመላ ዓለም የሚገኝ አጥቢ እንስሳ ወገን ነው። ረጃጅም የፊት ጥርሶች ካላቸው ዘራይጥ የሚባል የእንስሳት ክፍለመደብ አባል ናቸው። እነዚህ እንስሳት በተለያየ መጠን ሊገኙ ይችላሉ፤ ነገር ግን በዋነኛነት በፈጣን አካሄዳቸው፣ በረጅም ጅራታቸው እና በፀጉራም አካላታቸው ሊታወቁ ይችላሉ። Rattus በሚባል ወገን 64 ዝርያዎች ናቸው። በዋነኛነት ቡናማ አይጥ ወይም Rattus norvegicus እና ጥቁር አይጥ ወይም Rattus rattus ለሰው ልጆች ቀረቤታ አላቸው።

More information ?አይጥ, ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ ...
?አይጥ
Thumb
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: ጉንደ እንስሳ (Animalia)
ክፍለስፍን: አምደስጌ (Chordata)
መደብ: አጥቢ (Mammalia)
ክፍለመደብ: ዘራይጥ Rodentia
አስተኔ: የአይጥ አስተኔ Muridae
ወገን: አይጥ Rattus
ዝርያ: 64 ዝርያዎች
Close

ከዚህም ወገን ውጭ ብዙ ሌሎች እንስሶች ደግሞ «አይጥ» በስማቸው አላቸው። በተለይም ትንሽ አይጥ (Mus) የሚባለው የዘራይጥ ወገን 30 ዝርያዎች ናቸው፣ እሱም በዘልማድ «አይጥ» ይባላል።

«አይጠ መጐጥ» ልዩ ልዩ ትርጉሞች አሉት። አንዳንዴ ማናቸውም ትልቅ አይጥ «አይጠ መጐጥ» ቢባልም፣ በትክክል ግን «መጐጥ» እንዳጋጣሚ አይጥ በጣም የመሠለ እንጂ ዘራይጥ ያልሆነ ሌላ ፍጡር ነው።


Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.