ንግስት እሌኒ የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ሚስት ስትሆን ከንጉሱ ሞት በኋላ በሌሎች ሶስት ነገስታት ዘመን ከፍተኛ የአስተዳደር ስራ ፈጽማ በ1516ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት አርፋለች። የተቀበረችውም በትልቅ ጥበብ ባሰራችው ቤ/ክርስቲያን መርጡለ ማርያምጎጃም ነው።

እሌኒ የሃድያው ንጉስ መሐመድ ልጅ ስትሆን ዘርዓ ያዕቆብን ባገባች ጊዜ ክርስቲያን ሆናልች። አንዳንድ ታሪክ ጸሃፊያን (ለምሳሌ ባላዛር ቴሌዝ ፖርቱጋላዊው) ልጅ እንዳልነበራት ሲዘግቡ ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ ግን በልብነ ድንግል ዘመን አንዱ ወንድ ልጇ ከአምባ ግሸን አምልጦ እንደነበር መዝግቧል [1]

አጼ ዘርዓ ያዕቆብን የተካው ልጁ ቀዳማዊ አጼ ባእደ ማርያም እናቱ ጺዮን ሞገሴ በሞተች ጊዜ እንጀራ እናቱን እሌኒን እናት ንግስት ብሎ ሾማት። ማዕረጓን በሚያስከብር ሁኔት እኩል ከንጉሱ ዘንድ አገሪቷን እንዳስተዳደረች የታሪክ ተመራማሪወች ይጽፋሉ [2]። አጼ እስክንድር ባዕደማሪያምን ሲተካ እናት ንግስቲቱ ከቤተመንግስቱ እንድትገለል ራስአምደ ሚካኤል አድርጎ ነበር። በዚህ ምክንያት በ1486 ይህ ንጉስ ከስልጣን እንዲወርድ በተደረገው ሴራ ከተካፈለች በኋላ በማንኛውም የቤተመንግስት አስተዳደር ስርዓት ውስጥ እስከ እለተ ሞቷ ተካፍይ ሆናልቸ። በአጼ ናኦድ ጊዜም ከፍተኛ ተሰሚነት ነበራት።

ናኦድ ጦርነት ላይ ሲሞት ልብነ ድንግልን እሷ እና አቡነ ማርቆስ 8ኛ ንጉስ እንዳረጉት አልቫሬዝ መዝግቧል"[3] ። የፖርቹጋሉን ፔሮ ዳ ካቭላ ምክር በመስማት በዘመኑ እያየለ የሄደውን የኦቶማን ቱርኮች ሃይል ግምት ውስጥ በማስገባት ፖርቹጋሎች ለልብነ ድንግል እርዳታ እንዲያረጉ በምቲወስ በኩል መልዕክት የላከች ይችው ንግስት ነበረች [4] ። የልብነ ድንግል ዋና ሞግዚት ሆና ከእናቱ ናኦድ ሞገሴና ከወጣቱ ንጉስ ዘመድ የጎጃሙ ራስ ደሳለኝ በመሆን ልብነ ድንግል እድሜው እስኪ ጎለምስ አገሪቱን አስተዳድራለች።

በጎጃም ክፍል ሃገርም በጣም ሰፊ የሆነ ርስት እንደነበራት አልቫሬዝ ይዘግባል.[5]

አልቫሬዝ የሞተች ጊዜ የሆነውን ጉዳይ እንዲህ ሲል ዘግቧል፦

የንግስት እሌኒ መሞት ወሬ በሰፊው ይሰራጭ ነበር። ሰውም "እሷ ሳለች ሁላችንም መከታ እና ከለላ አግኝተን እንኖር ንበር ፣ እሷ ስትሞት ግን ትንሽ ትልቅ ሳንል ሁላችንም ሞተናል" ይላል።

በማለት ዘግቧል። በርግጥም እሌኒ ከሞተች ከ7አመት በኋላ የግራኝ ጦርነት ተነስቶ በሁዋላ እሱዋ በጠየቀችው የፖርቹጋሎች እርዳታ አገሪቱን መከላከል ተሽሏል።

ዋቢ ጽሁፎች

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.