From Wikipedia, the free encyclopedia
ኅዳር ፱ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፷፱ኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፺፯ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፺፮ ቀናት ይቀራሉ።
፲፬፻፹፮ ዓ.ም. - ክሪስቶፎሮ ኮሎምቦ የተባለው ኢጣልያዊ መርከበኛ በሰሜናዊ አሜሪካ ምሥራቃዊ ድንበር በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ የምትገኘውን የፑዌርቶ ሪኮ ደሴትን አገኘ።
፲፱፻፲፩ ዓ.ም. - በባልቲክ ባሕር የምትገኘው ላትቪያ ከሩስያ ነጻ የሆነች ሉዐላዊ አገር መሆኗን አወጀች።
፲፱፻፲፱ ዓ.ም. - በደብሊን አየርላንድ የተወለደው ታዋቂ የሥነ ጽሑፍ ሰው ጆርጅ በርናርድ ሾው በስነጽሑፍ የተሸለመውን የኖቤል ሽልማት ቢቀበልም ለዚሁ ሽልማት የተወሰነውን አንድ መቶ አሥራ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ስድሳ አምሥት የስዌድ ክሮና ግን አልቀበልም አለ። በኋላ ግን በገንዘቡ በስዌድ ቋንቋ የተጻፉ መጻሕፍት ወደ እንግሊዝኛ እንዲተረጎሙበት አደርገ። ጆርጅ በርናርድ ሾው የሽልማቱ አሸናፊነቱ ይፋ በሆነ ጊዜ፤ “አልፍሬድ ኖቤልን ዲናሚትን መፍጠሩን ይቅር ልለው እችላለሁ፤ ነገር ግን የኖቤል ሽልማትን ለመፍጠረ የሚበቃ ግን በሰው የተመሰለ ሰይጣናዊ መንፈስ ነው” አለ።
፲፱፻፷፱ ዓ.ም. - የእስፓኝ የሕዝብ ምክር ቤት፣ አገሪቱን ከ ሠላሳ ሰባት ዓመት የ”አምባገነን” መንግሥት ስርዐት በኋላ፣ ወደዴሞክራሲያዊ ስርዐት የሚያሸጋግር ህግ አጸደቀ።
2013
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.