የቨርሳይ ውል (1911 ዓም) ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ቀጥሎ ጀርመን ተሸንፎ ለአሸናፊዎቹ ሃያላት የተዋዋለው ስምምነት ውል ነበረ። የመንግሥታት ማኅበርም በዚህ ስምምነት ይቆም ጀመር።
በአውሮፓም ሆነ በቅኝ አገራት በኩል፣ ከጀርመን መንግሥት ብዙ ርስት ተነሣባት።
በአውሮፓ፦
- አልሳስ-ሎረን የተባለው ክፍል ወደ ፈረንሳይ ግዛት ተመለሰ።
- ኦይፐን-ማልመዲ የተባለው ሰፈር ወደ ቤልጅግ ግዛት ተጨመረ።
- በሽለስቭክ-ሖልሽታይን ዙሪያ ከሕዝብ ውሳኔ (1912 ዓም) ቀጥሎ ስሜኑ ወደ ዴንማርክ ተጨመረ።
- ሕሉቺንስኮ የተባለው ሰፈር ወደ አዲሱ ቸኮስሎቫኪያ ግዛት ተሰጠ።
- በሲሌስያ ዙሪያ ከሕዝብ ውሳኔ (1913 ዓም) ቀጥሎ ምሥራቁ ወደ አዲሱ ፖላንድ ግዛት ተጨመረ።
- ከምዕራብ ፕሩሺያና ከፖዘን አውራጆች ብዙ መሬት ለፖላንድ ተሰጠ። ምሥራቅ ፕሩሺያ ክፍልን ከተረፈው ጀርመን የሚያስለይ «የፖላንድ መተላለፊያ» ተሰጠ።
- ዳንፂክ ከተማ (የአሁኑ ግዳንስክ) በመንግሥታት ማህበር ሞግዚትነት ነጻ ከተማ-አገር ሆነ።
- መመል የተባለው ዙሪያ ለጊዜው በመንግሥታት ማህበር ሞግዚትነትና በፈረንሳይ ሥራዊት ጥብቅና ሆነ፤ በ1915 ዓም ግን የሊቱዌኒያ ሃያላት ወደ ግዛታቸው ያዙት።
- ዛዓር (ዛዓርላንት) የተባለው ክፍላገር ለጊዜው በአሸናፊ ሃያላት ሥራዊት አስተዳደር ሥር ሆነ። በ1927 ዓም ወደ ጀርመን (ናዚ ጀርመን) ተመለሰ።
- በተጨማሪ የጀርመን ምዕራብ ራይንላንት ክፍል በአሸናፊ ሃያላት ሥራዊት አስተዳደር እስከ 1922 ዓም ድረስ ቆየ።
በቅኝ አገራትም፦
የጀርመን ቅኝ አገራት ሁሉ ወዲያው ወደ መንግሥት ማህበር ጥብቅና በሞግዚትነቶች ተሰጡ።
- ቶጎላንድ እና ጀርመን ካሜሩን ወደ ፈረንሳይ (እና በከፊል ወደ ዩናይትድ ኪንግደም) ተዛወሩ።
- ጀርመን ምሥራቅ አፍሪካ ባብዛኛው (የአሁን ታንዛኒያ) ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ተዛወረ።
- የርዋንዳ-ኡሩንዲ ክፍል ወደ ቤልጅግ ተዛወረ።
- የኪዮንጋ ማዕዘን፣ በጣም አነስተኛ ሰፈር ወደ ፖርቱጋል ተዛወረ።
- በጀርመን አስተዳደር የነበረችው ጪንግታው ከተማ በቻይና ውስጥ ወደ ጃፓን ተዛወረች።
- ጀርመን ሳሞዓ የተባሉት ፓሲፊክ ደሴቶች ወደ ኒው ዚላንድ ተዛወሩ።
- ጀርመን ኒው ጊኒ እና ናውሩ ደሴት ወደ አውስትራሊያ ተዛወሩ።
- ከምድር ወገብ ስሜን የተቀመጡት ሌሎችም የተለያዩ የጀርመን ደሴቶች የደቡብ ፓሲፊክ ሞግዚትነት ተብሎ ወደ ጃፓን ተዛወሩ።
ከዚህም በላይ በጀርመን መንግሥት ላይ በጣም ትልቅ ካሳ ክፍያና እጅግ ብዙ አስቸጋሪ ቅጣት ድንጋጌዎች ተበዙበት። እነዚህ ከባድ ኹኔታዎች ለአዶልፍ ሂትለርና ለናዚ ጀርመን ጠንቅ እንደ ሆኑ ተብሏል።
Wikiwand in your browser!
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.