ባላ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ባላ (ፓራቦላ) በሂሳብ ጥናት ውስጥ የተስተካከለ የባላ ቅርጽ ያለው የሂሳብ መስመር ነው ቃል ነው። ባላ በሂሳብ እንዲህ ሲደረግ የፈጠራል፡ ባንድ ጠፍጣፋ ሜዳ ላይ አንድ ነጥብና አንድ መስመር እንውሰደ። ለዚህ ነጥብ እና ለመስመሩ እኩል ርቀት ላይ የሆኑ ነጥቦቹን በሜዳው ላይ ብንደረድር የምናገኘው ስዕል ባላ/ፓራቦላ ይሆናል ማለት ነው። ነጥቡ ፎከስ ሲባል፣ መስመሩ ዳይሬክትሪክስ ይባላል።
- ይህ መጣጥፍ ስለ ሥነ ሂሳባዊው መስመር ነው። ለሰዶም ንጉሥ፣ ባላ (የሰዶም ንጉሥ) ይዩ።
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/am/thumb/3/31/ParabolaAnimate.gif/300px-ParabolaAnimate.gif)
አረንጓዴው ዳይሬክትሪክስ የምንለው ቀጥተኛ መስመር ነው
የላይኛው ሰማያዊ መስመር የሚመነጭበት ነጥብ ፎከስ ይባላል
የሁለቱ ሰማያዊ መስመሮች ርዝመት እኩል ነው። ስለዚህ ቀዮቹ ነጥቦች ከአረንጓዴው ቀጥተኛ መስመርና ከፎከሱ ነጥብ እኩል ርቀት ስላሉ ቀዩ ባላ (ፓራቦላ) ነው እንላለን