From Wikipedia, the free encyclopedia
«ባለሙያ ንድፍ» (እንግሊዝኛ፦ Intelligent design) በተለይ በአሜሪካ አገር የጀመረ የዝግመተ ለውጥ አከራካሪ አስተያየት ነው። በዚህም አስተሳሰብ የ«ዝግመተ ለውጥ» እና የ«ተዓምር» (የእግዚአብሔር ሥራ) ትርጉም አንድ ነው።
ዓለሙ በ«ባለሙያ ንድፈኛ» መፈጠሩ ለእግዚአብሔር ሕልውና ማስረጃ ያህል መሆኑ በእርግጥ ጥንታዊ አስተያየት ነው። እንዲህ ያለ ሃሣብ እንኳ በሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ እንደ ተጠቀሱ በጅሮንድ ተክለ ሐዋርያት «ፈጣሪ መኖሩንና የበላይ ገዥነቱን የሚያሳምነን ዓለምን በሙሉ በማይፈርስና በጽኑ ሕግ ለዘላለም ወስኖ በመፍጠሩ ነው» ብለዋል። ጃንሆይም በራሳቸው በኩል እጅግ ብዙ ተመሳሳይ አስተያየቶች ይናገሩ ነበር።
በአሜሪካ አገር የሕዝቡን መብቶች ለመጠብቅ፣ በ1783 ዓም የአሜሪካ ሕገ መንግሥት ፩ኛ መለወጫ እንዳለ በከፊል፦ «ስለ ሃይማኖት መመሥረት የነካ፣ ወይንም የእርሱን ነጻ ተግባር የከለከለ ሕግ ምክር ቤቱ አይሠራም...።» የዚህ ላይኛ ሕግ አሣብ ምንም የመንግሥት ሃይማኖት እንዳይመሠረት፣ እንዲሁም መንግሥት በሃይማኖታዊ ጉዳይ ጥልቅ ከማለት ለመከልከል እንዲደረግ ነበር።
በ19ኛው ክፍለ ዘመን ቻርለስ ዳርዊን የዝግመተ ለውጥ ሃልዮ ባሳተመ ወቅት በመጀመርያ በሃይማኖታዊ ሰዎች ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት አላገኘም ነበር፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ዘንድ እግዚአብሔር ከ6 ሺ ዓመት በፊት ዓለሙን በ፮ ቀናት ውስጥ እንደ ፈጠረ ይመስላልና።
እስካሁን ድረስ ይህ ክርክር ባይፈታም ለከሃዲዎች ወገን ብዙ ተስፋ ሰጣቸው፤ «መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ የተሳተ ቢሆንስ ዓለሙ ፈቃዶቻችንም ምናልባት ያለምንም ፈጣሪ ዝም ብለው እንዳጋጣሚ ከአንዳችም ታይተዋል» በማለት ገመቱ። ይህ አይነት ጥርጣሬ አስተያየት በጣም ረቂቅ ግሩም ዓለማችን ወይም ነጻ ፈቃዳችን ለምን ወይም እንዴት ከአንዳችም እንደ ደረሱ ግን አይገልጽልንም፤ ብዙ የማይፈቱ ጥያቄዎች ከመተዉ በላይ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ በማስተዋል የተሳተ ነው በጭራሽ ለማለት እንዲህ ቀላል አይሆንም። ኦሪት ዘፍጥረት ፩ እንደሚለው፣ ከመጀመርያው ቀን በኋለ ምንም ጠፈር ወይም ፀሐይ ገና አልነበሩም፤ የነበረው ውሃ፣ ብርሃን፣ እና የእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ ናቸው። መሬት በዚህ ቀን ከተገኘች፣ በውኃው ውስጥ መሆን ነበረበት እንጂ ጠፈር ወይም ፀሓይ ገና ሳይኖሩ የ«ቀን» ትርጉም እዚህ የመሬት 24 ሰዓታት መዞር ሊባል እንደ ቻለ አይመስልም። በእግዚአብሔር አስተያየት አንድ ቀን መባሉ ብርሃኑ ከውሃ ዙሪያ ለመጓዝ የፈጀበት ጊዜ ሊሆን ይቻላል። ከሳይንሳዊ ግመት በመተንተን እንግዲህ ይህ መጀመርያ «ቀን» ምናልባት 9 ቢሊዮን የኛ የምድር ዓመታት እንደ ሆነ ይቻላል።
ከ፪ኛ ቀን በኋላ፣ አብዛኛው ውኃ ደርቆ ጠፈር ተፈጠረ፣ የቀረው ውኃ ተለይቶ ለምድርና ለአንዳንድ ሌላ ዓለም ይጠብቅ ነበር። ይህ «ቀን» ደግሞ ያለ ፀሓይ ብዙ ቢሊዮን አመታት ሊሆን ይችላል።
ከ፫ኛ ቀን በኋላ፣ ውኃው በምድር በይበልጥ ደርቆ የብስ ተገለጠ፣ የብስም የአትክልት ወገን አስገኘ። በሳይንሳዊ ግመት ደግሞ ምንም እንስሳ ሳይኖር አትክልት በመላው የብስ ላይ ተስፋፍቶ ነበር። በዚህ አስተያየት ይህ «ቀን» ምናልባት ብዙ መቶ ሚሊዮን ዓመታት ቆየ።
ከ፬ኛው ቀን በኋላ፣ ጸሐይ እና ጣቢያው በሙሉ በሥፍራ ተገኝቶ ነበር። ዳሩ ግን በሳይንሳዊ ግመት አትክልት የብሱን ከመሸፈኑና ጉንደ እንስሳ ከመታየቱ መካከል ብዙ መቶ ሚሊዮን ዓመታት ስላሉ፣ ይህም ቀን እንደኛ ቀን ዛሬ ነበር ማለት ያስቸግራል።
ከ፭ኛው ቀን በኋላ፣ የባሕር እንስሳትና ተሳቢ አራዊት እስከ አዕዋፍ ድረስ ተፈጥረዋል። ባለፈው ቀን አትክልት የተገኙ ከየብስ ሲሆን፣ አሁን ግን የእንስሶችን ወገን ያስገኘው ውኃው ይባላል። አጥቢ እንስሳትና በመጨረሻ የሰው ልጅ ግን በሚከተለው ፮ኛው ቀን የተፈጠሩ ነው። የሰው ልጅም በተረፈው ዓለም ላይና በእንስሶች ላይ ላዕላይነትና ገዥነት ተሰጠ። ይህም ሁሉ ከሳይንሳዊው አስተሳሰብ በቅድመ ተከተል ረገድ እጅግ አይለይም፤ ቀኖቹ ግን ብዙ መቶ ሚሊዮን ዓመታት እንደ ፈጁ ይላል። እግዚአብሔር የአብርሃም ልጆችን ከድንጋይ በኃይሉ ማምጣት ከቻለ (ማቴ. 3:9)፣ በእርግጥ የበራሂ ኮድ ዐውቆአል ማለት ነው፤ ከጦጣ በራሂ አራያ ለውጦ የሰው ልጅን አራያ በራሂ ፈጥሮ (2a+b = 2) አዳም ግን ከጦጣ መወለዱ አስፈላጊ አልነበረም ማለት ነው፤ ከጦጣ ተወለደ ብንል ኖሮ ግን «ምድር ያስገኘው ፍጥረት» መባሉ እንኳ ውሸት አይሆንም ነበር። ከዚያ በኋላ ሰብአዊ ነፍስና አዕምሮ ተቀብሎ በዚያን ጊዜ ሰው «እግዜር ከመሬተ ምድር ያስገኘው ፍጥረት» ሆነና እግዜር ሰዎችን መፍጠሩ «መልካም እንደ ሆነ አየ» መባሉ ቁም ነገር ነው።
ያም ሆነ ይህ ይህን ሁሉ ቸል ብለው «መጽሐፍ ቅዱስ ተሳተና ስለዚህ ይህ ሁሉ አለምና ሕያው ነፍስ ሕይወትም እንዳጋጣሚ ከአንዳችም ታዩ» የሚል የከሃዲ ወገን በየጥቂቱ ተቀባይነቱን ያስፋፋ ጀመር። የዝግመተ ለውጥ ትምህርት በመጨረሻ በአሜሪካ መንግሥት ትምህርት ቤቶች እንዲገባ ከተፈቀደ በኋላ፣ ጥቂት ዓመታት አልፈው የሥነ ፍጥረት ትምህርት ለማስወገድ የጣረ እንቅስቃሴ ተነሣ።
በ1979 ዓም የአሜሪካ ላይኛ ችሎት ፈራጆች ይን ሃሣብ ተረድተው የሥነ ፍጥረተኛ ትምህርት ከአሜሪካ መንግሥት ትምህርት ቤቶች እንዲከለከል በየኑ። ለዚያው ብያኔ መሠረት፣ ሕገ መንግሥቱ የመንግሥት ሃይማኖትን ስለማይፈቅድ፣ የአገሩ ምክር ቤት ይቅርና ትምህርት ቤት ስንኳ ምንምን ሃይማኖት ለመደግፍ አይፈቀድምና ዝግመተ ለውጥ ከከሃዲነት ጋራ ማስተምር ተገደዱ አሉ።
ከዚህ ቀጥሎ የ«ባለሙያ ንድፍ» ሃሣብ ዘመናዊነት አገኘ። በተለይ በአሜሪካ ሰፊ ሕዝብ መካከል፣ ላይኛ ችሎቱ ሥነ ፍጥረት ከትምህርት ቤት ምንም ቢያስወግድም፣ ከግማሽ በላይ የክርስትናንና የመጽሐፍ ቅዱስ አማኞች ናቸው።
ነገር ግን የ«ባለሙያ ንድፍ» ክርክር እንደገና በ1998 ዓም በአንድ የአሜሪካ ችሎት ቀርቦ፣ ፈራጁ የከሃዲነትን ወገን ደግፎ አለሙ በማናችም «ባለሙያ ንድፈኛ» ከቶ አልተነደፈም በማለት በየነ፤ ወይም ይህ አስተሳሰብ ሳይንሳዊ ስለማይሆን በትምህርት ቤት አይፈቀድም፤ በመንግሥት ትምህርት ቤት ከሃዲነት ብቻ ይታገሣል ማለት ነው።
በአውሮፓ ኅብረት መንግሥት ደግሞ ከከሃዲነት በቀር ይህ አሣብ ምንም ሳይታገስ በፍጹም ይከለከላል። በእስልምናና በሂንዱኢዝም አገራት ዘንድ ግን፣ ዓለም የ«ባለሙያ ንድፍ» ነው የሚል ሃሣብ ለትምህርት ሳይንሳዊ መሆኑ ትኩረትና ተቀባይነት አገኝቷል።
ብልሃት ከሰው ልጆች የሚወጣ ሲሆን ጥበብ ሁሉ ከፈጣሪ ይወጣል። የሰው ልጅ ብልሃት ሲዳከም የፈጣሪ ጥበብ ሊረዳን የሚቻለው ነው። «ባለሙያ» ለሮማይስጡ intelligent ሲተረጎም በዚሁ ረገድ ይህ ባለሙያነት የፈጣሪ ጥበብ እንጂ የሰው ልጅ አይነት ብልሃት አይሆንም። እግዚአብሔር እኛን ከጡት አጥቢዎች የሠራን ከድሮ ጀምሮ ቢታወቅም፣ ይህ የሆነው ምድሪቱ «የእግዚአብሔር መረገጫ» እንዲል (ኢሳ. ፷፮፡፩፣ ማቴ ፭፡፴፭) ለመፈጸም በማሠብ ሆን ብሎ ተደረገ ማለቱ ነው።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.