በእውቀቱ ስዩም
From Wikipedia, the free encyclopedia
በእውቀቱ ስዩም በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ገጣሚያንና ደራሲያን አንዱ ነው። በተለይም ኮሜዲ አዘል በሆኑ መጣጥፎቹ ይታወቃል። በአዲስ ላይቭ ኢንተርኔት ሬዲዮ በሚያቀርባቸው ትረካዎቹም ታዋቂነትን አትርፏል። በሲዲ በተለቀቁ የኮሜዲ ሥራዎች ላይም እንደ ደረጀ? እና ሌሎች ታዋቂ ኮሜዲያን ጋር ተሳትፎ አለው።
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/am/e/ec/Bewqetu.jpg)
“ኗሪ አልባ ጎጆዎች”፣ “በራሪ ቅጠሎች” እና “የእሳት ዳር ሀሳቦች” የተባሉ የግጥም መጻኅፍት ሲኖሩት እነዚህን በአንድ ላይ አሰባስቦ “ስብስብ ግጥሞች” ብሎ አሳትሟል። ከዚህ በተጨማሪ “መግባትና መውጣት”፣ “እንቅልፍና እድሜ” እንዲሁም በ2008 ዓ.ም. ባወጣው “ከአሜን ባሻገር” በተሰኙ ሥራዎቹ ይታወቃል።