From Wikipedia, the free encyclopedia
ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) መጀመርያ ከ1819 እስከ 1816 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የንግሥት ሶበክነፈሩ ተከታይ ነበረ።
==
1 ሶበክሆተፕ | |
---|---|
ምናልባት የሶበክሆተፕ ራስ ምስል፤ መታወቂያው እርግጥኛ አይደለም | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1819-1816 ዓክልበ. |
ቀዳሚ | ሶበክነፈሩ |
ተከታይ | ሰኸምካሬ ሶንበፍ |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
አባት | 4 አመነምሃት? |
==
መቃብሩና ብዙ ቅርሶች በቅርቡ (2005 ዓ.ም.) ተገኝተዋል። የቶሪኖ ቀኖና በተባለው ፈርዖኖች ዝርዝር መሠረት በዚሁ ሥርወ መንግሥት በ19ኛው ሥፍራ ነገሠ፤ የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልት ከሥነ ቅርስ ሰነዶች እንደሚያስረዳው ግን፣ በመጀመርያ ሥፍራ ከሶበክነፈሩ ቀጥሎ እንደ ነገሠ ይመስላል። አባቱ «አመነምሃት» ሲባል በራይሆልት አስተሳሰብ ይህ 4 አመነምሃት ሳይሆን አይቀርም። ስለዚህ ሶበክነፈሩ አክስቱ ትሆናለች።
በእርሱ ዘመን የ14ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያ ፈርዖን ያክቢም ሰኻኤንሬ በአባይ ወንዝ አፍ ዙሪያ ለእርሱ ተገዥ ሆኖ ነገሠ። እነዚህ ከከነዓን የደረሱ ሴማዊ እረኞችና ነጋዴዎች ነበሩ። በጤቤስ ፈርዖኖች ፈቃድና ስምምነት ግዛታቸው በስሜን ግብጽ የንግድ ማዕከል ሆነ፤ ይህም በብሉይ ኪዳን ጌሤም የተባለው ሀገር ነው። ግብጽ እንደገና ተከፋፍሎ ይህ ወቅት የመካከለኛው መንግሥት መጨረሻ እና የ፪ኛው ጨለማ ዘመን መጀመርያ ይቆጠራል።
ቀዳሚው ሶበክነፈሩ |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን | ተከታይ ሰኸምካሬ ሶንበፍ |
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.