ሰኔ ፮ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፸፮ኛው ቀን ሲሆን የፀደይ (በልግ)ወቅት ፸፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፺ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፹፱ ቀናት ይቀራሉ።


ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፲፱፻፳፮ ዓ/ም - የናዚያዊ ጀርመን መሪ አዶልፍ ሂትለር እና የፋሺስታዊ ኢጣልያ መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ በኢጣልያን ከተማ ቬኒስ ላይ ተገናኙ። ከግንኝነታቸው በኋላ ሙሶሊኒ በሂትለር ላይ በማሾፍ “ኮስማና ሞኝ ጦጣ” ብሎታል። (“ጀበናዋ ድስትን ሻንቅላ ብላ ሰደበች” እንደሚሉ!)
  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ከሰኔ ፮ - ፲፯ የተካሄደው ሁለተኛው የነፃ አፍሪቃ አገሮች ስብሰባ አዲስ አበባ ላይ ሲከፈት ከሁለት መቶ ሃምሣ በላይ ልዑካን እና ተመልካቾች ተሳትፈዋል።
  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የንግድ ሚኒስትር አቶከተማ ይፍሩ የተመራ የሰባት ኢትዮጵያውያን ልዑክ ለአሥራ ሁለት ቀን የንግድ ውይይት ወደቻይና መዲና ቤይጂንግ አመራ።
  • ፲፱፻፺፪ ዓ/ም - የኢጣልያ መንግሥት ግንቦት ፭ ቀን ፲፱፻፸፫ ዓ/ም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን ጳጳስ ዳግማዊ ዮሐንስ-ጳውሎስን በጥይት ያቆሰለውን ቱርክ፣ ሜህመት አሊ አጅካን (Mehmet Ali Agca) በምኅረት ከእስር ለቀቀው።

ልደት

  • ፲፱፻፸፬ ዓ/ም - ኢትዮጵያዊው ሯጭ ቀነኒሳ በቀለአርሲ ክፍለ-ሀገር በቆጂ ከተማ ላይ በዚህ ዕለይ ተወለደ።

ዕለተ ሞት


ዋቢ ምንጮች

  • (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/June_13
  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836 - Annual Report from Ethiopia for 1960
  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1660 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1973


More information የኢትዮጵያ ወራት ...
Close

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.