ሚያዝያ ፳፫
From Wikipedia, the free encyclopedia
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴፫ኛው ዕለት ሲሆን የፀደይ (በልግ)ወቅት ፳፰ተኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፻፴፫ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፻፴፪ ዕለታት ይቀራሉ።
ሚያዝያ ፳፫
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይሄንን ዕለት ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሞተበትን ዕለት ማስታወሻ አድርጋ ትዘክረዋለች፡
“በዘአዕረፈ እግዚእየ ማር ጊዮርጊስ ገብሩ ለኢየሱስ ክርስቶስ በዘተከለለ ወርኁ በጽርዕ ጵንፍልዮ ስሙ ዘበትርጓሜሁ ሚያዝያ አመ ፳ወ፫ ለሠርቅ ወዕለቱሂ ዓርብ በጊዜ ፱ቱ ሰዓት አሜን።”
“የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ጌታዬ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያረፈበት ሰማዕትነቱን የፈጸመበት ወሩ በጽርዕ ጵንፍልዮ ይባላል። ይኸውም ሚያዝያ ነው ወሩ በባተ በሃያ ሦስት ቀን ዕለቱም ዓርብ በዘጠኝ ሰዓት ነው አሜን።” [1]