መስከረም ፲፩ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፲፩ ኛው ዕለት እና የክረምት ፹፪ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፶፭ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፶፬ ዕለታት ይቀራሉ።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፯፻፹፭ ዓ/ም በፈረንሲስ የዘውድ ስርዓት ተሽሮ አገሪቱ ሪፑብሊክ ሆነች።
- ፲፱፻፵ ዓ.ም - የክቡር ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ አጽም በስደት ዘመን አርፈው ከተቀበሩበት ከእንግሊዝ አገር ወደ ውድ አገራቸው ኢትዮጵያ ተመልሶ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተቀበረ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የሥራ ሚኒስትር ከአሜሪካ ጉዟቸው ሲመለሱ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት ቦይንግ ፯መቶ፳-ቢ (Boeing 720B) ጄት አውሮፕላኖች መግዣ እና ለቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የሚውል ብድር ከ ኤክሲም ባንክ (Export Import Bank) ጋር የስምምነት ውል መፈራረማቸውን ይፋ አደርጉ።
- ፳፻፪ ዓ/ም በምዕራብ ጐጃም የአንድነት ቅርንጫፍ ቢሮ አስተባባሪዎች ላይ ድብደባ ተፈጸመ
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836 - Annual Report from Ethiopia for 1960
Wikiwand in your browser!
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.