ሃሪ ፖተር ክፍል ስድስት (ፊልም)
እ.ኤ.አ 2009 ዓ.ም ለዕይታ የበቃ ፊልም / From Wikipedia, the free encyclopedia
ሃሪ ፖተር ክፍል ስድስት (English: Harry Potter and the Half Blood Prince; ጥሬ ትርጉሙ: ሃሪ ፖተርና የግማሽ ደም ልዑሉ) እኤአ ፳፻፱ ዓም ለዕይታ የበቃ የብሪቲሽ ፊልም ነው። ፊልሙ በሃሪ ፖተር ተከታታይ ፊልሞች ውስጥ ስድስተኛው ክፍል ሲሆን በዴቪድ የትስ ዳይሬክት ተደርጎ በስቲቭ ክሎቭስ ተፅፎ እንዲሁም በዋርነር ብሮስ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።
Quick Facts
ሃሪ ፖተር ክፍል ስድስት |
|
ርዕስ በሌላ ቋንቋ | Harry Potter and the Half-Blood Prince (እንግሊዘኛ) |
ክፍል(ኦች) | ስድስተኛ |
የተለቀቀበት ዓመት | 15 ጁላይ 2009 እ.አ.አ. |
ያዘጋጀው ድርጅት | ዋርነር ብሮስ (Warner Bros. Pictures) |
ዳይሬክተር | ዴቪድ የትስ (David Yates) |
አዘጋጅ | ዴቪድ ሀይማን (David Heyman) ዴቪድ ባሮን (David Barron) |
ምክትል ዳይሬክተር | {{{ምክትል_ዳይሬክተር}}} |
ጸሐፊ | ሮውሊንግ (J. K. Rowling) |
ሙዚቃ | ኒኮላስ ሁፐር (Nicholas Hooper) |
ኤዲተር | ማርክ ደይ (Mark Day) |
ተዋንያን | ዳኒኤል ራዲክሊፍ (Daniel Radcliffe) ሩፐርት ግሪንት (Rupert Grint) ኢማ ዋትሰን (Emma Watson) ራልፍ ፊነስ (Ralph Fiennes) ሚካኤል ጋምቦን Michael Gambon) ጂም ብሮድቤንት (Jim Broadbent) አለን ሪክማን (Alan Rickman) ቶም ፌልተን (Tom Felton) ሄሊና ቦንሃም (Helena Bonham) ካርተር (Carter) እና ሌሎችም |
የፊልሙ ርዝመት | 153 ደቂቃ |
ሀገር | እንግሊዝ አሜሪካ |
ወጭ | 250 ሚሊዮን ዶላር |
ገቢ | 933,959,197 ዶላር |
ዘውግ | {{{ዘውግ}}} |
የፊልም ኢንዱስትሪ | ሆሊውድ የእንግሊዝ ፊልም ኢንዱስትሪ |
Close
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
ይህ ፊልም "Harry Potter and the Half Blood Prince" በተሰኘው በፀሀፊ ጄ.ኬ ሮውሊንግ የተፃፈውና እ.ኤ.አ በ፳፻፭ ዓም ለህትመት በበቃው መፅሀፍ ተመስርቶ የተሰራ ሲሆን ፊልሙ የሚተርከውም ሃሪ ፖተር ስድስተኛ የትምህርት አመቱን በሆግዋርትስ የአስማተኛ ትምህርት ቤት የሚያሳልፈውን ጊዜንና የሎርድ ቮልድሞርትን የመርቻ ቁልፍ ስራ የሚሰራበትን ኩነት ነው። እ.ኤ.አ በ፲፭ ጁላይ ፳፻፱ ዓም ሲኒማ ቤትን የረገጠው ይህ ፊልም በተመልካቾችና በሐያስያን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቷል። የዚህ ተከታይ ፊልም ሃሪ ፖተር ክፍል ሰባት በኖቬምበር ፳፻፲ ዓም ለዕይታ በቅቷል።