From Wikipedia, the free encyclopedia
አቃቢነት ወይንም ካፓሲታንስ የሚለካው የአንድ ቁስን የኤሌክትሪክ ሙላት (ቻርጅን) የማጠራቀም ችሎታ ነው። የበለጠ ትክክል ለመናገር አንድ ቁስ ላይ በሚያርፍ የቮልቴጅ ጫና ምክንያት ያ ዕቃ ሊያጠራቅመው የሚችለው የኤሌክትሪክ ሙላት መጠን የዚያ ቁስ አቃቢነት ይባላል። ስለሆነም አቃቢነት በአንድ ቁስ ውስጥ የሚገኝ የኤሌክትሪክ ሙላት እዚያ ዕቃ ላይ በተጫን ቮልቴጅ ሲካፈል ይገኛል፡፡ በሒሳብ ቋንቋ፦
መለኪያውም ፋራድ farad ሲሰኝ 1 ፋራድ 1 ኩሎምብ ሙላት በ1 ቮልት ማለት ነው።
አቃቢነት በኤሌክትሪክ ዑደት ስራ ላይ ተፈላጊ እንዲሁ ያልተፈለገ ባህሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ተፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እራሳቸውን ይቻሉ አቃቢዎች በተፈለገው መጠን ዑደቱ ውስጥ ይገባሉ።
አንድ አቃቢ ለመስራት የሚያገለግሉ ኤሌክትሪክ አስተላላፊዎች፣ ጂዎሜትሪያቸው ከታወቀና በነዚህ አስተላላፊዎች መካከል ያሉ ኤሌክትሪክ አጋጅዎች የ ዳይኤሌክትሪክ ጸባይ ቁጥር ከታወቀ የአቃቢው ዋጋ ምን ሊሆን እንዲችል መተንበይ ይቻላል። ለምሳሌ የ"ትይይዩ ሳህን" አቃቢን ብንወስድ፣ ሳህኖቹ ስፋታቸው A ቢሆን፣ በመካከላቸው ያለው ክፍተት ርዝመት d ቢሆን፣ ከኒህ ሳህኖች የተሰራ አቃቢ ዋጋው እንዲህ ይሰላል
እዚህ ላይ
አቃቢነት እንግዲህ ከሳህኖቹ ተነባባሪ ስፋት ጋር እኩል ሲያድግ፣ በሳህኖቹ መካከል ከሚፈጠረው ክፍተት ርዝመት አንጻር የተገላቢጦች ያድጋል ማለት ነው።
በአቃቢ ውስጥ ሙላት ሲጠራቀም፣ አቅም ም ይጠራቀማል። የዚህ የተጠራቀመ አቅም መጠን እንዲህ ይሰላል፦
W የተጠራቀመው አቅም ሲሆን ; C አቃቢነት; እና V ቮልቴጅ ናቸው።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.