From Wikipedia, the free encyclopedia
ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ ሯ
ርእስ በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ 20ኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ ፊደሎች በሶርያም 20ኛው ፊደል «ሬስ» ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል «ራእ» ተብሎ በ«አብጃድ» ተራ 20ኛ ነው።
የርእስ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የራስ ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። አጠራሩ ግን «ተፕ» ነበር። በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው «ሬስ» ስላሉት፣ ይህ ስዕል "ር» ሆኖ እንዲሰማ መጣ።
የከነዓን «ሬስ» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ «ሬስ» የአረብኛም «ራእ» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት ፊደል «ሮ» (Ρ, ρ) አባት ሆነ። እሱም የላቲን አልፋቤት (R r) እና የቂርሎስ አልፋቤት (Р р) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ«ርእስ» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር ፻ (መቶ) ከግሪኩ ρ በመወሰዱ እሱም የ«ረ» ዘመድ ነው።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.