ሜሪላንድ
From Wikipedia, the free encyclopedia
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሜሪላንድ (እንግሊዝኛ፦ Maryland) በአሜሪካ የምትገኝ ስቴት ስትሆን ምዕጻረ ቃሏ MD ወይም Md. ነው። ሜሪላንድ ከአሜሪካ አስራሶስት ጥንታዊ ስቴቶች አንዷ ናት። ከሜሪላንድ ጋር የሚገናኙ ስቴቶች ፔንስልቫኚያ ፣ ቨርጂኚያ ፣ ዌስት ቨርጂኚያ ፣ እና ዴላዌር እያሉ፤ ደግሞ በኮለምቢያ ክልል (ዋሽንግተን ዲ.ሲ.)ና በአትላንቲክ ውቂያኖስ ትወሰናለች። የቼሳፒክ ወሽመጥ ስቴቱን መሃል ለመሃል ይከፍለዋል። የሜሪላንድ ከፍተኛ ቦታ የባክቦን ተራራ ጫፍ ነው። የሜሪላንድ አየር ሁኔታ ከቦታ ቦታ ይለያያል። የምስራቅ ክፍሉ ሞቃታማ በጋና መካከለኛ ክረምት የአየር ሁኔታ ሲኖረው የምዕራብ ክፍሉ ደግሞ መካከለኛ በጋ እና በጣም ቀዝቃዛ ክረምት አለው። የሜሪላንድ ጠቅላላ ምርቶች በ2003 እ.ኤ.ኣ. ወደ 212 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ነው። በዚሁ ዓመት የአንድ ሰው የዓመታዊ ገቢ በኣማካይ 37,446 የአሜሪካን ዶላር ነበር ፣ ከአገሩ 5ኛ። ከፍተኛ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣ ወታደራዊ ካምፖች እና የሳይንስና የሕክምና ተቋማት በዚሁ ክፍላገር ይገኛሉ። የስቴቱ ዋና ያውሮፕላን ማረፊያ ባልቲሞር-ዋሽንግተን ዓለም አቀፍ ያውሮፕላን ማረፊያ (BWI) ነው። በ1996 የሜሪላንድ ጠቅላላ የህዝብ ብዛት 5,558,058 ነው ተብሎ ይገመታል። ከዚሁ ውስጥም 583,900ቹ ወይም 10.6 በመቶ ሌላ ስቴት ወይም አገር የተወለዱ ነዋሪዎች ናቸው። አብዛኛው ህዝብ የስቴቱ መዓከላዊ ክፍል ውስጥ ይኖራል።
| |||||
ዋና ከተማ | አናፖሊስ | ||||
ትልቋ ከተማ | ባልቲሞር | ||||
አገረ ገዥ | ማርቲን ኦማሊ | ||||
የመሬት ስፋት | 32,160 ካሬ ኪ.ሜ.(ከአገር 42ኛ) | ||||
የሕዝብ ብዛት | 5,296,486(ከአገር 19ኛ) | ||||
ወደ የአሜሪካ ሕብረት የገባችበት ቀን |
April 28,1788 እ.ኤ.ኣ. | ||||
ላቲቲዩድ (ኬክሮስ) | 37"53'N እስከ 39"43'N | ||||
ሎንግቲዩድ (ኬንትሮስ) | 75"4'W እስከ 79"33'W | ||||
ከፍተኛው ነጥብ | 1,024ሜ. | ||||
ዝቅተኛው ነጥብ | 0ሜ. | ||||
አማካኝ የመሬት ከፍታ | 105ሜ. | ||||
ምዕጻረ ቃል | MD | ||||
ድረ ገጽ | www.maryland.gov |
የህዝቡ የዘር ክፍልፋይ
የሐይማኖት ክፍልይ
ካውንቲ | የተመሠረተበት ዓ.ም.(እ.ኤ.ኣ.) | የመንግስት መቀመጫ |
አለገኒ ካውንቲ | 1789 | ከምበርላንድ |
አን አረንዴል ካውንቲ | 1650 | አናፖሊስ |
ባልቲሞር ካውንቲ | 1659 | ታውሰን |
ካልቨርት ካውንቲ | 1654 | ፕሪንስ ፍሬድሪክ |
ካሮላይን ካውንቲ | 1773 | ዴንተን |
ካሮል ካውንቲ | 1837 | ዌስትሚንስትር |
ሲሲል ካውንቲ | 1672 | ኤልክተን |
ቻርልስ ካውንቲ | 1658 | ላ ፕላታ |
ዶርቸስተር ካውንቲ | 1668 | ኬምበሪጅ |
ፍሬደሪክ ካውንቲ | 1748 | ፍሬደሪክ |
ጋሬት ካውንቲ | 1872 | ኦክላንድ |
ሀርፎርድ ካውንቲ | 1773 | ቤል ኤር |
ሀዋርድ ካውንቲ | 1851 | ኤሊኮት ሲቲ |
ኬንት ካውንቲ | 1642 | ቼስተር ታውን |
ሞንትጎመሪ ካውንቲ | 1776 | ሮክቪል |
ፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ | 1695 | አፐር ማርልቦሮ |
ክዊን አን ካውንቲ | 1706 | ሴንተርቪል |
ሴንት ሜሪ ካውንቲ | 1637 | ለናርድታውን |
ሶመርሰት ካውንቲ | 1666 | ፕሪንስስ አን |
ታልቦት ካውንቲ | 1662 | ኢስተን |
ዋሽንግተን ካውንቲ | 1776 | ሄገርስታውን |
ዊኮሚኮ ካውንቲ | 1867 | ሳሊስበሪ |
ዎርስተር ካውንቲ | 1742 | ስኖው ሂል |
|
|
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.