ጥቅምት ፭ ቀን
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፴፭ኛው ዕለት እና የመፀው ፲ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፴፩ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፴ ዕለታት ይቀራሉ።
- ፲፯፻፩ ዓ/ም - ከ፪ዓመት በፊት በዚህ ዕለት ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱን (ስመ መንግሥት አድያም ሰገድ) የገደሉትን ጳውሎስ እና ደርመንን ንጉሥ ዓፄ ቴዎፍሎስ የስቅላት ሞት ፍርድ ፈረዱባቸው።
- ፲፱፻፶፯ ዓ.ም. - የቀድሞዋ የሶቪዬት ሕብረት መሪ የነበሩት ኒኪታ ክሩስቼቭ ከሥልጣን ተሽረው፣ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት በአሌክሲ ኮሲጊን፤ በኮሙኒስት ፓርቲ ሊቀመንበርነት ደግሞ በሌዮኒድ ብሬዥኔቭ ተተኩ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የቀድሞው ንጉሠ ነገሥት የልጅ ልጅ መቶ-ዓለቃ ልዑል መኮንን መኮንን ትምህርት ላይ ከነበሩበት ከአሜሪካ ወደአገራቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱ ደርግ ትዕዛዝ አስተላለፈ።
- ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. - የቀድሞዋ የሶቪዬት ሕብረት መሪ የነበሩት ሚካይል ጎርባቾቭ የኖቤል ሰላማዊ ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ይፋ ተደረገ።
- ፲፮፻፺፱ ዓ/ም - በዓፄ ተክለ ሃይማኖት (ስመ መንግሥት ልዑል ሰገድ) ትዕዛዝ፣ ሸሽተው ጣና ሐይቅ ላይ በጨቅላ መንዞ ደሴት የነበሩትን አባታቸውን ዳግማዊ ኢያሱ አድያም ሰገድን ጳውሎስ እና ደርመን የተባሉ ነፍሰ ገዳዮች ሕይወታቸውን ካጠፉ በኋላ አስከሬናቸውን በእሳት አቃጠሉት። ከቃጠሎ የተረፈውን ካኡናቱ በታንኳ ወስደው ምጽራሓ ደሥተ ላይ ቀበሩት።
- ፲፱፻፴፱ ዓ.ም. - በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወንጀለኛነቱ የሞት ቅጣት የተፈረደበት ኸርማን ጎሪንግ ለቅጣቱ መፈጸሚያ ጥቂት ሰዐታት ሲቀሩ ሳያናይድ መርዝ በመውሰድ ራሱን ገደለ
- {{en]] P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
- {{en]] "All Nobel Peace Prizes". Nobelprize.org. 14 Oct 2011
http://www.nobelprize.org/nobel_prizes/peace/laureates/
More information የኢትዮጵያ ወራት ...
Close