ጣኔዎስ
From Wikipedia, the free encyclopedia
From Wikipedia, the free encyclopedia
በግሪኩ ታኒስ ከግብጽኛ ስም ጃነት ወይም ጃን መጣ።
በዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ «ጾዓን» ሲባል በግሪኩ ትርጉም (70 ሊ.) «ታኒስ» ይባላል። ብዙ ጊዜ በአገናዛቢው τάνεως ስለሚታይ፣ በብዙዎች እንደ ቦታው ስም ተቀበለ። በአማርኛውም ትርጉም «ጣኔዎስ» ከዚህ እንደ ደረሰ ይመስላል፣ በኩፋሌ ግን አንዴ «ጣይናስ» ተብሎ ይጻፋል።
በኦሪት ዘኊልቊ 13፡22 «ጾዓን» ከኬብሮን በኋላ 7 ዓመት ተሠራች ሲል ይህ ማለት በሂክሶስ ዘመን ዋና ከተማቸው የሆነው አቫሪስ ሳይሆን አይቀርም። በኋላ ዘመን ከዚህ አጠገብ ፈርዖኑ 2 ራምሴስ አዲስ ዋና ከተማ ፒ-ራምሴስ አሠራ።
ከ1085 ዓክልበ. ግድም ጀምሮ ፈርዖኑ ስመንዴስ ከፒ-ራምሴስ ሥፍራ በ25 ኪሎ. ርቀት ከሆነው ከአዲስ ዋና ከተማ «ጃነት» (ታኒስ) ገዛ። «ታኒስ» ወይም ጣኔዎስ በትክክል ለዚያው ሥፍራ ይጠቀማል፣ ለቀደሙት ዋና ከተሞች አቫሪስንና ፒ-ራምሴስን ይዩ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.