From Wikipedia, the free encyclopedia
ጀርመናዊ ቋንቋዎች የሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ቅርንጫፍ ሲሆን፣ ሁላቸው ከቅድመ-ጀርማንኛ ደረሱ።
የጀርመናዊ ቋንቋዎች ፫ ክፍሎች ምዕራብ ጀርመናዊ፣ ስሜን ጀርመናዊ፣ እና ምሥራቅ ጀርመናዊ ሲሆኑ ከነዚህ አንዱ ምሥራቅ ጀርመናዊ አሁን ጠፍቶ አይገኝም።
ዋና ቋንቋዎቹ እንግሊዝኛ፣ ሆላንድኛ፣ እና ጀርመንኛ ሲሆኑ፣ በነዚህ ውስጥ አያሌ ንዑስ ቀበሌኞች አሉ። ምዕራብ ጀርመናዊ ቋንቋዎች ይዩ።
እነዚህ ሁላቸው ከጥንታዊ ኖርስኛ ደረሱ። አሁን ዋናዎቹ ኖርዌይኛ፣ ስዊድኛ፣ ዳንኛ፣ አይስላንድኛ፣ ፋሮኛ ናቸው።
እነዚህ ቋንቋዎች አሁን አይገኙም። ጎትኛ፣ የክሪሜያ ጎትኛ፣ ቫንዳልኛ፣ እና ቡርጉንድኛ ምሥራቅ ጀርመናዊ ልሳናት ነበሩ።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.