From Wikipedia, the free encyclopedia
ኦሪት ዘፍጥረት የመጽሐፍ ቅዱስ፣ የብሉይ ኪዳንና የኦሪት የመጀመሪያው መፅሐፍ ነው።
በዚሁ መጽሐፍ ከሥነ-ፍጥረት፣ የዔድን ገነት ጀምሮ እስከ ዮሴፍ ዕረፍት በጌሤም ድረስ ይተረካል። በተለይ ለአብርሃም፣ ለወላጆቹና ለተወላጆቹ ትኩረት ይሰጣል።
በልማድ መሠረት፣ እንደ ሌሎቹ የኦሪት መጻሕፍት፣ የመጽሐፉ ደራሲ ወይም አቀነባባሪ ሙሴ እንደ ነበር ይባላል። እንዲሁም ሌላው መጽሐፍ፣ መጽሐፈ ኩፋሌ ስለነዚህ ታሪኮችና ዘመኖች ሲተርክ፣ መላዕክት ለሙሴ በደብረ ሲና በቀጥታ እንዳቀረቡት ይላሉ። በኦሪት ዘፍጥረት ውስጥ ካለው መረጃ፣ ግማሹ ያህል ከኩፋሌ ውስጥ ደግሞ ይገኛል። በዘፍጥረት ውስጥ ሌላው ግማሽ ካልታወቁት ምንጮች ወይም ጥንታዊ ልማዶች ሊሆኑ ይቻላል።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.