ኤችአይቪ
From Wikipedia, the free encyclopedia
From Wikipedia, the free encyclopedia
ኤች አይቪ ኤድስ በሚኖርበት ጊዜ ቫይረሱ የሰውነትን የበሽታ መከላከያ በተለይ የነጭ ደም ሴሎችን (ህዋሳትን) በማጥቃት በቀላሉ ሰውነት ለበሽታ እንዲጋለጥ የሚያደርግ ቫይረስ ነው። ኤችአይቪ ያለባቸው ሰዎች የበሽታው ምልክት ሳይታይባቸው ለብዙ ዓመታት መኖር ይችላሉ። ቫይረሱ በሰውነታ ውስጥ እስከ አስር ዓመት በመቆየት ምንም ሳይታውቅ እና ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳይታይበት በመኖር እና አለማውቅ ከአንድ ሰው ወደሌላ ሰው ሊተላለፍ የሚችል አደገኛ ቫይረስ ነው።
ኤችአይቪ የሚያጠቃው የሰውነት የነጭ የደም ሴሎችን የሰውነት የበሽታ የመከላከያ ተቁዋማትን ነው። የሲዲፎር በመባል የሚታውቀውን የሰውነት የነጭ የደም ሴል ቁጥሩን (cd4 count) ከ 200 በታች በማድረግ የቫይረሱ መጠን በደም ውስጥ እንዲጨምር በማድረግ ለሕይወት ኣደገኛ እና ምቹ ጊዜ ተባቂ በመባል የሚታውቁትን በሸታዎች (ኦፓርቹንስቲክ ኢንፈክሽስ Opportunistic infections) OIs. በመፍጠር ኤድስ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያደርጋል።
ኤድስ ማለትም ኣኳየርድ ኢምዩኖደፊሸንሲ ሲንድረም ሲሆን ኤድስ ኤችእይቪ የማያማጣው የመጨረሻ ደረጃ ነው። ኤችአይቪ ያለበት ሰው ኤድስ ደረጃ ላይ ለመድረስ ብዙ ዓመታት ይወስድበታል። እንዲሁም መድኃኒቱንም ሳይጅምር ኤድስ ደረጃ ሳይደርስ ብዙ ዓመታት ሊቆይ ይችላል። አንድ ሰው የኤድስ ደረጃ ላይ ደረሰ ማለት የኤችአይቪ ቫይርስ የበሽታ መከላከያ ሃይል ተቁዋማትን ደምስሶ እና ሰውነታችን ከማንኛውም በሽታ የመቋቋም ኃይሉን በማሳጣት ለተለያዩ ኢንፈክሽኖች ይጋለጣል። አንድ ሰው አንድ ወይም ሁለት ኢንፌክሽኖች ሲኖሩበት እና በጣም ዝቅያለ የቲ-ሴል ቁጥር ሲኖረው ያሰው የኤድስ ደረጃ ደረሰ ሊያስብለው ይችላል።
ሳይንቲስቶች የኤችአይቪን ቫይረስ አመጣጥ እንደጠቆሙት ከሆነ ከዌስት አፍሪካ ከሚገኝው ቺፓንዝ ዝርያ የመጣ መሆኑን አሳወቀዋል። ይህውም ሊሆን የቻለው የሰው ልጅ ቺፓንዚን ለምግብነት በሚይድንበት ጊዜ በሚደረገው የደም ንክኪ መሰርት ቫይርሱ ሊተላለፈ እንደቻለና። ከብዙ አመት በሃላም ቀስ በቀስ ወደ መላው አለም ሊስፋፋ እንደቻለ ገልጽዋል ኤችአይቪ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ የመጣው ከ1978 (፲፱፻፸ ዓ.ም.) ወዲህ ነው። በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ውስጥ 1.3 ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ሰዎች ከኤችአይቪ ቫይርስ ጋር አብረው ይኖራሉ። በዓለም ላይም ከ 25 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኤድስ በሚመጣ በሸታ ተይዘው ሞተዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዬጵያ ውስጥ የኤድስ ታማሚዎች መኖራችው የተረጋገጠው በ1978 ዓ/ም ነው። በ2006ዓ/ም ወደ 2.9 ሚሊዮን የሚጠጉ ወንዶች፤ ሴቶች እና ሕጻናትም ሕይወታቸውን አተዋል። ኤችአይቪ ከተያዙት ውስጥ ከግማሸ በላይ የሚገምቱት ሲሞቱ 39.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ከቫይርሱ ጋር በመኖር ይገኛሉ። በቅርቡ በUNAIDS/WHO እንደተዘገበው 4.3 ሚሊዮን የሚጠጉ አዲስ ሰዎች በኤችአይቪ እንደተያዙ ይገልጻል።
ከኤችአይቪ ቫይረስ ለመከላከል የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይጠቅማል
-በጣም አስጊ ደረጃ ላይ ሊሆኑ የሚችሉ
እርግጠኛ ዕራስን ለማወቅ ግዴታ መልሱ የሚገኘው የኤችአይቪ ምርመራ በማድረግ ብቻ ነው። ስለዚህ ዕራሶን የሚጠራጠሩ ከሆነ ተመርመሩ። ተመርምረው ውጤቶን ከቫይረሱ ነፃ መሆኖ ቢነገሮትም የውሽት ውጤት የሚባል (ዊንዶ ፔሬድ የሚባል) ነገር ስላለ ከ 3-6 ወር በሃላ እርግጠኛ ለመሆን ደግመው መመርመር ይገባል። ይህን ሲያረጉ ግን አሁንም ኮንዶም መጠቀሞን አይርሱ።
ኤችአይቪ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ የመጣው ከ1978 (፲፱፻፸ ዓ.ም.) ወዲህ ሲሆን እስከ 1985 ድረስ የተበከለ ደም ናሙና በመወጋትና በመሳሰሉት ብዙ ሰዎች ይዚህ ሰለባ በመሆን ብዙ ሰዎች ተይዘዋል። ከ1988 ወዲህ ግን ኤችአይቪ ሲኖር ደም ውስጥ ነጭ ሴል የሚሠራውን ኣንቲቦዲ (Antibody) በመመርመር ኤችአይቪ ቫይረስ እንዳለ እና እንደሌለ የሚጣራበት ፈጣን የምርመራ ዘዴ ስለተሠራ በሆስፒታል ከሚሰጠን ደም መተላለፉ ቀርትዋል።
ከአካል የሚወጡ ፈሳሾች ላይ ሁሉ ኤችአይቪን ማግኝት የሚቻል ቢሆንም መደበኛ የኤችአይቪ ምርመራ በደም ናሙና ላይ የሚደረግ የኤችአይቪ-1/2 አንቲ ባዲ ምርመራ ነው።
እስታሁን የተሰሩትን የአንቲባዲ ምርመራ አይነቶችን በሁለት ከፍል ማየት ይቻላል።
ኤላይዛ መሰረት አርገው የሚከናወኑ
ፈጣን ምርመራዎች የሚባሉት ተመርተው በገበያላይ የቀርቡ ወደ 60 የሚቆጠሩ መመርመሪያዎች ሲኖሩ በሶስት ዋና ዋና ቴክኒኮች ላይ የተመረኮዙ ናችው።
እነዚህ መመርመሪያዎች እያንዳንዳቸው ለምርመራ ማከናወኛነት በምንጠቀምበት ጊዜ ምንም አይነት ተጨማሪ ኪሚካል አያስፈልጋቸውም።
ለመጠቀምም ጊዜ የማይፈጅና ዋጋውም ተመጣጣኝ ነው። አስተማማጝነታቸውም ከኤላይዛር ጋር የሚስተካከል ነው።
ፈጣን የኤችአይቪ ምርመራ ማለት ለቫይረሱ የተዘጋጀ አንቲ ቦዲ በደም ውስጥ መኖሩንና አለመኖሩን የሚያመልክት የምርመራ አይነት ነው። በፈጣን የምርመራ ዘዴ ውጤቱን ከ10-60 ደቂቃዎች ውስጥ ማውቅ የሚያስችል የመመርመሪያ ዘዴ ነው።
በአሁኑ ጊዘ በኤችአይቪ ዙሪያ ላይ በዙ መረጃዎች የሚገኘበት ግዘ ስለሆነ ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖርይቻላል። በአሁን ሰአት ኤችአይቪን እንደማንኛውም አይንት ቫይረስ አይቶ ጤናን እየጠበኩና መንፈስን ሳያስጨንቁ ተረጋግቶ መኖር ይቻላሉ።
ኤችአይቪ እንዳይዘን የምንከላከልበት ክትባት በአሁኑ ሰአት የለም። ኤችአይቪ ከያዘም በኋላ የሚፈውስ መድኃኒት የለም። ነገር ግን ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖር የቻላለ። በአሁኑ ጊዜ ፀረ-ኤችአይቪ መዳኒቶች ከፈተኛውን አስታውጾ በማድረግ ላይ የገኛሉ። ኤችአይቪ ያለበት ሰው በትክክል የፀረ-የኤችአይቪ መዳኒቶቹን በመውሰድ እንደማንኛውም ሰው መኖር ይችላል። ቫይርሱ ያለባቸው ሰዎች መውለድ ሲፈልጉ ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ከጤና ባለሙያቸው ጋር በመነጋገር ጤነኛ ልጀ መውለስ ይችላሉ። ኤችአይቪ ያለባት እናትከማርገዝዋ በፊት ማወቅ የሚገባትን ቅድመ ተከተሎች መከተል ይኖርባታል።
ኤችአይቪ እንዴት እንደሚተላለፍ መረጃዎችን በመከታተል ቫይረሱ እንዳይሰራጭ ትክክለኛዎቹን ጥንቃቄዎች መከተልና ለሌሎችም ማስተማር የያንዳንዳችን ኃላፊነት መሆን አለበት። ኤችአይቪ እንዴት እንደሚተላለፈ ግንዛቤዎች እንዴት እንደምንከላከል መረዳትና ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ እንዴት መጠንቀቅ እንዳለብን ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነው።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.