ኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ

From Wikipedia, the free encyclopedia

ኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ

ብርሃን ፍጥነት የሚጓዙ ሞገዶች ኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ ይሰኛሉ። እያንዳንዳቸው ሞገዶች እርስ በርሳቸው ቀጤ ነክ(ፐርፔንዲኩላር) የሆኑና በአንድ ቅድሚያ (ፌዝ) የሚርገበገቡ የኤሌክትሪክ መስክ እና የመግነጢስ መስክ አላቸው። ሁለቱም መስኮች በተራቸው ሞገዶቹ ለሚጓዝበት አቅጣጫ ቀጤ ነክ ናቸው።

Thumb
የኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ ስፔክትረም (አይነቶች)

የኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ በሚኖረው የሞገድ ድግግሞሽ ይከፈላል። ከዝቅተኛ ድግግሞሽ ተነስቶ ወደ ከፍተኛ ድግግሞሽ ሲዘረዘር፣ በጣም ዝቅተኛው የኤሌክትሮመግንጢስ ጨረራ ድግግም የራዲዮ ሞገድ ሲሆን፣ ከዚያ ማይክሮዌቭታህታይ ቀይ፣ በሰው ዓይን የሚታይ ብርሃንላዕላይ ወይንጸጅኤክስ ሬይ ይልና ከሁሉ ከፍተኛ ድግግሞሽ ያለውን ጋማ ጨረርን በመያዝ ይጠቀለላል።

እነዚህ የብርሃን ወንድሞች በተፈጥሯቸው ከብርሃን ጋር አንድ ቢሆኑም ፣ የሰው ዓይን ሊያያቸው ስለማይችል ብርሃን አይባሉም። ሆኖም ግን አንድ አንድ እንስሳት እነዚህን ሞገዶች መመልከት ይችላላሉ። ለምሳሌ ታህታይ ቀይ የሚባለው የብርሃን ታናሽ ወንድም፣ ለሰዎች እንደ ሙቀት ሆኖ ይሳመላ። ለምሳሌ የፀሐይ መሞቅ ከምትተፋው የታህታይ ቀይ ጨረራ ይመነጫል። በበረሃ የሚንከላዎሱ እባቦች ይህን ሞገድ በአይናቸው መመልከት ስለሚችሉ፣ ሙቀት ያለውን ማንኛውንም ነገር በጭለማ ሳይቀር ማየት ይችላሉ። ንቦች በተቃራኒ፣ የሰው ልጅ እማያየውን ላዕላልይ ወይን ጠጅ ሞገድ በዓይናቸው ማየት ስለሚችሉ፣ አበቦች ለንቦች ከሰው ልጅ የተለየ መልክና መልዕክት ያስተላልፋሉ።


የኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ፣ ከሞገድነት ባሻገር የእኑስነት ባህርይም ያሳያል። የጨረራው መሰረታዊ እኑስ ፎቶን ሲባል ለሞገዱ ጉልበት ተሸካሚ ነው። በአጠቃላይ መልኩ ማናቸውም የኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ አቅም እና እንድርድሪት አለው፤ መኖር ብቻ ሳይሆን ይህ አቅምና እንድርድሪት ወደ ቁስ አካላት ሊሻገር ይችላል።

የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት (ፊዚክስ)

ኅልዮት

ጸባዮች

ሞገዳዊ ሞዴል

እኑሳዊ ሞዴል

የጉዞ ፍጥነት

የሙቀት ጨረራ እና ኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ የሙቀት አይነት ስለመሆኑ

ኤሌክትሮመግነጢስ ስፔክትረም

Thumb
ማውጫ:
γ = ጋማ ጨረራ
HX = ጠንካራ ኤክስ ሬይs
SX = ለስላሳ ኤክስር ሬይ
EUV = ኃይለኛ ላዕላይ ወይንጸጅ
NUV = ቅርብ ላዕላይ ወይንጸጅ
በዓይን የሚታይ ብርሃን
NIR = ቅርብ ታህታይ ቀይ
MIR = መካከለኛ ታህታይ ቀይ
FIR = ሩቅ ታህታይ ቀይ

ራዲዮ ሞገዶች:
EHF = በጣም እጅግ ከፍተኛ ተደጋጋሚ (ማይክሮዌቭ)
SHF = እጅግ ከፍተኛ ተደጋጋሚ (ማይክሮዌቭ)
UHF = ልዩ ከፍተኛ ተደጋጋሚ
VHF = በጣም ከፍተኛ ተደጋጋሚ
HF = ከፍተኛ ተደጋጋሚ
MF = መካከለኛ ተደጋጋሚ
LF = ዝቅተኛ ተደጋጋሚ
VLF = በጣም ዝቅተኛ ተደጋጋሚ
VF = ድምጽ ተደጋጋሚ
ULF = ልዩ ዝቅተኛ ተደጋጋሚ
SLF = እጅግ ዝቅተኛ ተደጋጋሚ
ELF = በጣም እጅግ ዝቅተኛ ተደጋጋሚ

ብርሃን

ብርሃን

ራዲዮ ሞገድ

ሂሳባዊ ቀመር


ዋቢ መጻሕፍት

የውጭ ማያያዣ

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.