ቅጠሎቹ እና ዘሮቹ በብዙ አበሳሰሎች ውስጥ ቅመሞች ናቸው። የአብሽ ዘሮች ወይንም ዱቄቱ በአገር ቤት ገበያ ይታያል።
ዱቄቱ ወደ ማር ሲጨመር ለጥሩ መጠጥ ይደረጋል። መጠጡ ሞርሟሪ ሲሆን ክብደት ለመጨመር ይረዳል ተብሏል። እንዲሁም እንደ ቡና ሊፈላ ይችላል።
አብሽ ከባቄላ ተቀቅሎ ለብጉንጅ ህክምና ይውላል። ተወቅጦ ወይም ልሞ በእብጠቱ ላይ ይለጠፋል።
በቁምጥና፣ በጡንቻ በሽታ፣ በቁርጥማጥ ላይ ጥቅሙ ተዘግቧል።[1]
የአብሽ ዘሮችም ለስኳር በሽታ እንደሚረዳ በኢትዮጵያ ይታመናል።[2] በ2008 በተደረገ ትንተና ዘንድ፣ ተጨማሪ ምርመራ ያስፈልጋል ብለዋል።[3]
ፍሮንስ ከበደ
Gong, J; Fang, K; Dong, H; Wang, D; Hu, M; Lu, F (2 August 2016). "Effect of Fenugreek on Hyperglycaemia and Hyperlipidemia in Diabetes and Prediabetes: a Meta-analysis". Journal of Ethnopharmacology 194: 260–268. doi:10.1016/j.jep.2016.08.003. PMID 27496582.