አቡነ ዮሴፍ ተራራላሊበላ በስተስሜን ምስራቅ የሚገኝ፣ ከኢትዮጵያ በከፍታው 16ኛ የሆነ ተራራ ነው። ከባህር ወለል በላይ 4260ሜትር የሚደርሰው ይህ ከፍተኛ ቦታ ከአካባቢው ጠለል ደግሞ በ1909 ሜትር ወደላይ ይጎናል። አቡነ ዮሴፍ ተራራ መቼና መድኃኔ አለምን፣ይምርሃነ ክርስቶስን፣ ጀመዱ ማርያምን፣ ገነተ ማርያምን፣ አሸተን ማርያምንና ሌላ አንድ የአለት ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናንን በማቀፍ በታሪክ ይታወቃል። የእንግሊዙ አርኪዮሎጂ ተማሪ ክራውፎርድ የጨረቃ ተራራ ተብሎ በጥንቶቹ ግሪኮችና አረቦች የሚታወቀው ጀበል ኤል-ካማር ይህ ተራራ እንደነበር ያስረዳል[1]። የጨረቃ ተራራ (ጀበል ኤል ካማር) በኋላ ኢኩየተር በመባል ለምድር ወገብ ስሙን የለገሰ ሐረግ ነው።

Quick Facts
አቡነ ዮሴፍ
Thumb
ጭላዳ ዝንጀሮ በአቡነ ዮሴፍ ተራራ
ከፍታ 4260ሜትር
Thumb
{{{alt}}}
አቡነ ዮሴፍ

12°9′ ሰሜን ኬክሮስ እና 39°10′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

Close

የተፈጥሮ ቅርስ

በአቡነ ዮሴፍ ተራራ ላይ በተደረገ ጥናት የ43 አይነት አጥቢ እንስሳት መኖሪያ መሆኑ ሲረጋገጥ፣ 221 አይነት ወፎችም ቤታቸው አድርገው ይኖሩበታል። ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙት ጭላዳ ዝንጀሮ እና ቀይ ተኩላ በዚሁ ቦታ ይገኛሉ ። አቡነ ዮሴፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የአዕዋፍ መኖሪያዎች በወፍት ሃብቱ ሁለተኛ ነው[2]


ካርታ

ማጣቀሻ

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.