From Wikipedia, the free encyclopedia
ነጥሮን በጥንት እንደ ሳሙና የጠቀመ ማዕድን ነው። የአምቦ አመድ ጨው አይነት ሲሆን ውሃ አዘል ሶዲየም ከሰላ ነው።
ነጥሮን በጥንት በተለይ በጥንታዊ ግብፅ ከደረቁት ሐይቆች ወለል ይወሰድ ነበር። ለልብስና ሰውነት ሳሙና ጥቅም ከዘይት ጋር ይቀላቀል ነበር። ከዚህ በላይ ለአፍ ማጠቢያ፣ ለፀረ-ሕዋስ መድኃኒት፣ አሣን ወይም ሥጋን ለመጠበቅ፣ ጠፍርን በመፋቅ፣ እንዲሁም ግብጻውያን ሬሳ እንዳይፈርስ ሲጠብቁ በተጠቀሙት መድኃኒት ውስጥ ነጥሮን ይጨመር ነበር። በሸክላም ሆነ በብርጭቆ ውስጥ ሲጨመር ደግሞ ሰማያዊ ቀለም ለመስጠት ነበር።
ቃሉ ነጥሮን፣ በዓረብኛ /ናጥሩን/፣ በግሪክኛም /ኒትሮን/፣ በአካድኛ /ኒትሩ/፣ በአራማይክ /ኒጥራ/፣ በዕብራይስጥ /ኔቴር/፣ በግብጽኛ /ነጨሪት/ ሆነ። «ነጨሪት» በግብጽኛ ደግሞ «የተነጠረ፤ የአምላክ» ማለት ሲሆን ከ
/ነጨር/ ወይም «አምላክ» ነው። በአማርኛና ግዕዝ ቃሉ «ንጥር» በጥንተ ንጥር፣ እድገንጥር እና ንጥር ቅቤ ደግሞ ከዚህ ጽንሰ ሐሣብ ጋር ይዛመዳል።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.