From Wikipedia, the free encyclopedia
ቴሌቪዥን የስዕል እና ድምጽ ምልክቶችን ከማሰራጫ የሚቀበል የመገናኛ ዘዴ ነው። «ቴሌ-» የሚለው ክፍል በግሪክ «ሩቅ» ማለት ቢሆን «-ቪዥን» ደግሞ ከሮማይስጥ visio /ዊዚዮ/ «ማየት» («ትርዒት») ተወስዷል። በአጠቃላይ ቴሌቪዥን ማለት ተንቀሳቃሽ ምስልን (ብዙ ጊዜ ከድምፅ ጋር) ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማስተላለፍ የሚረዳ የመልዕክት ማስራጫ መንገድ ነው። ይህ ከሆነ ዘንዳ ቴሌቪዥን ምስል መቅጃውንም ሆነ ምስል መቀበያውን መሳሪያ ሁሉ ያጠቃልላል ግን በተለምዶ ቴሌቪዥን የምንለው ምስል መቀበያውን ብቻ ነው።
በ1873 እ.ኤ.አ. (1865 ዓም) የእንግላንድ ኤንጅኔር ውሎቢ ስሚስ ባደረገው ጥረት ጥንተ ንጥሩ ሴሌኒይም ብርሃን-አስተላልፎሽ መሆኑን ገለጸ።
በ1884 እ.ኤ.አ. ፓውል ጎትሊብ ኒፕኮው የተባለ ጀርመናዊ ክብ የሆነ ዲስክን በስፓይራል በምብሳት ይህ ዲስክ በተሽከረከረ ቁጥር ከፊትለፊቱ የሚመጣውን ብርሃን በቀዳዶቹ በማሾለክ ከሴሌኒይም በተሰራ የካሜራ ግድግዳ ላይ እንዲያርፍ አደረገ። ግድግዳው ብርሃን ሲነካው ያንን ብርሃን ወደ ኮሬንቲ ሃይል በመቀየር ምስልን በኮሬንቲ መልክ በሽቦ ለመላክ ቻለ። ነገር ግን በዚህ ጊዜ አምፕሊፋየር ስላልነበር የሚላከው ምስል እምብዛም አመርቂ አልነበረም።
ከ27 አመታት በኋላ በ1911 እ.ኤ.አ. የራሻው ቦሪስ ሮዚንግ ለመጀመሪያ ጊዜ የሲርቲን ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ አሁንም ለመጀመሪያ ጊዜ ተንቀሳቃሽ ምስልን ለመላክና ለመቀብል ቻለ። ነገር ግን የሚንቀሳቀሱት ምስሎች የጂዎሜትሪ ቅርጽ ነበራቸው ማለትም ሶስት ማዕዘን፣ አራት ማእዘን ወዘተ...
ከ7 አመታት በኋላ በ1925 እ.ኤ.አ. ጆን ሎጂ ቤርድ የተሰኘው የስኮትላንድ ተመራማሪ 2ቅጥ ያላቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመላክ ቻለ ከዚያም በ1926 እ.ኤ.አ. ጥቁርና ነጭ የሆኑ ምስሎችን ለማስተላለፍ በቃ። በዚህ ጊዜ የሚላኩት ምስል ጥራት 30 መስመር በአንድ ጊዜ ነበር፣ በዚህም ምክንያት የሰውን ፊት ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ግን ይቻል ነበር። አቶ ቤርድ በጥር 18 ቀን 1918 ዓ.ም. (26 January 1926 እ.ኤ.አ.) የመጀመሪያውን የቴሌቪዥን መግለጫ ሰጠ።
በ1927 እ.ኤ.አ. ኸርበርት አይቭስ የተሰኘው የቤል ላብራቷር ተቀጣሪ 16 የምስል ገጽታ በሰከንድ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኒውዮርክ ከተማ በሽቦ መላክ ቻለ። ቀጠል አድርጎም በራዲዮ ወደ ዊፓኒ ኒው ጀርሲ ለመላክ በቃ። በዚያው አመት ፊሎ ፍራንስዎርዝ የመጀመሪያውን የተሟላና በኤሌክትሪክ ስካኒንግ ብቻ የሚስራውን የቴሌቭዥን ስርዓት በተግባር አዋለ።.በጥር 1928 እ.ኤ.አ. (1920 ዓም) መጀመርያው የቴሌቪዥን ማሰራጫ ጣቢያ በስከነክተዲ፣ ኒው ዮርክ ተከፈተ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ያሰራጫል።
በርግጥም የመጀመሪያው በሰፊው ተግባራዊ የሆነ የቴሌቭዥን ስርዓት ስራ ላይ የዋለው በጀርመን አገር ሲሆን ይኸውም በ1929 እ.ኤ.አ. ነው። በ1936 እ.ኤ.አ. (1928 ዓም) ጀርመን ሃገር ተደርጎ የነበረውን የኦሎምፒክ ውድድር በቴሌቭዥን ሊሰራጭ ቻለ፣ ህዝቡም ውድድሩን እቤቱ ሆኖ ቀጥታ ሲካሄድ ለማየት ቻለ።
ከዚያ መጀመርያው ጥቁርና-ነጭ ፕሮግራሚንግ በዩናይትድ ኪንግደም 1928 ዓም፤ በአሜሪካ 1933 ዓም ተደረገ። በአፍሪካ መጀመርያው ጣቢያዎች በ1952 ዓም በናይጄሪያና ደቡብ ሮዴዝያ (አሁን ዚምባብዌ) ተሰራጩ፣ በኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ስርጭት አገልግሎት (ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን) የጀመረው በ1956 ዓም ሆነ።
ሁለት አገራት - እነርሱም ቱቫሉና ኪሪባስ - ምንም የራሳቸውን ቴሌቪዥን አሁን አያሰራጩም፤ ሆኖም የሌላ አገር ስርጭት እዚያ ሊታይ ይችላል።
ከዚያ ቤርድ በግንቦት 26 ቀን 1920 (ጁላይ 3, 1928 እ.ኤ.አ.) የመጀመሪያውን የከለር ቴሌቪዥን ስርጨት ሙከራ አደረገ።
ነገር ግን ከለር ቴሌቪዥን ቢፈጠረም ለሚከተሉት ብዙ ዓመታት ስርጭት ባብዛኛው ጥቁርና ነጭ ብቻ ሆኖ ቀረ። ይሄው ቴክኖዎሎጂው በጣም ውድ፣ በጣም ከባድና በትክክል ያልተስተካከለ ስለ ሆነ ነው። በየጥቂቱ ከ1946 ዓም (1954 እ.ኤ.አ.) ጀምሮ አገራት ወደ ከለር ስርጭትና ከለሩን ማሳየት የሚችል ቴሌቪዥን ወደ መሸጥ ይዛወሩ ጀመር። በጥር ወር 1946 ዓም NBC የተባለው አሜሪካዊ ስርጭት ጣቢያ በከፊሉ ወደ ከለር ተሸጋገረ፤ ብዙ ሰዎች ግን ያንጊዜ ከለር ማሳያ ቴሌቪዥን ለመግዛት ገና አልቻሉም ነበር። ከ1955 እስከ 1959 ዓም ድረስ ሌሎቹ ትልልቅ አሜሪካዊ ጣቢያዎች ABC እና CBS ደግሞ ወደ ከለር ተዛወሩ፣ የከለርም ተቀባዮች ዋጋ እየተቀነሰ የሚይዩት ሕዝብ ቁጥር ደግሞ ከዚህ በኋላ እየተጨመረ ሄደ፤ ከረጅሙ ጥቁርና-ነጭ ዘመን ቀጥሎ ከለርም በኅብረተሠብ ያመጣው ለውጥ ለግዙፍነቱ በኋላ ኢንተርኔት እንደ ሆነ ያሕል ነው።
ጃፓን በ1952 ዓም፣ ሜክሲኮ በ1955፤ ካናዳ በ1958፣ የአውሮፓ ኅብረትና የሶቪዬት ሕብረት በ1959፣ ኮት ዲቯር በ1962፣ አውስትራሊያ በ1967 ከለር ስርጭትን ጀመሩ። በኢትዮጵያም ከለር ስርጭት ከ1976 ዓም ጀምሮ ተገኝቷል። በ1977 ዓም ሮማኒያ ከጥቁርና-ነጭ ስርጭት ወደ ከለር ማሰራጨት የለወጠ በዓለም መጨረሻው ሃገር ሆነ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.