From Wikipedia, the free encyclopedia
ቡታጅራ የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልልና የጉራጌ ዞን ከተማና ልዩ ወረዳ ነው። በመስቃን ወረዳ ይከበባል።
ቡታጅራ የመብራት ኃይል፣ የስልክና የፖስታ ቤት አገልግሎት ካሉዋቸው ከተሞች አንዱ ነው። የብታጅራ ገበያ በየዓርቡ ይካሄዳል።
ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት የተቀደሠ ምንጭ አለ፤ የከተማ መስጊድ ደግሞ በ1972 ዓም ተሠራ።
በ1918 ዓም ሚስዮኑ ፔር አዛዕዝ በሥፍራው ምንም አላገኘም። በ1927 ዓም ግን አንድ ጀርመናዊ ጉዞ ከተማው የጉራጌ አገር መቀመጫ ሆኖ እንደ ተመሠረተ አመለከተ። በ1929 ዓም ጣልያኖቹ ራስ ደስታ ዳምጠውን በቡታጅራ ገደሉዋቸው። በ1933 ዓም አርበኞችና የብሪታንያ ጭፍሮችም ከተማውን ነጻ አወጡት።
የሕዝብ ቁጥር በ1999 ዓም በ33,406 ሰዎች ተቆጠረ።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.