ሹዱሩል
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሹ-ዱሩል ወይንም ሹ-ቱሩል ከ2001 እስከ 1986 ዓክልበ. ግድም የአካድ መጨረሻ ንጉሥ ነበረ።
በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ከዱዱ ቀጥሎ ለ፲፭ ዓመት እንደ ነገሠ ይዘግባል። ሆኖም ለእርሱ ዘመን አንዳችም «የዓመት ስም» አልተረፈልንም።
እንደ አባቱ ዱዱ ዘመን ጉታውያን በጠቅላላው መስጴጦምያን ሠፍረው የሹዱሩል ግዛት ከአካድ ከተማ እንዳልራቀ ከጥቂት ቅርሶች ብቻ ሊታወቅ ይቻላል። ከአካድ ከተማ ጭምር ቱቱብና ኤሽኑና ይገዛ ነበር። ከዚያ በላይ አሁን ዲያላ ወንዝ የሚባለው በዚያን ጊዜ «ሹዱሩል ወንዝ» በሚለው ስም ይታወቅ ነበር።[1]
በዝርዝሩ ዘንድ ከሹዱሩል በኋላ አካድ ተሸነፈና የመስጴጦምያ ላዕላይነት ከአካድ ወደ ኡሩክ (ኦሬክ) ተዛወረ። ከዚያ ስድስት የኡሩክ ነገሥታት ይዘርዝራል። ሆኖም ከነዚህ ፮ የአንዳችም ኅልውና በሥነ ቅርስ ገና አልተረጋገጠም። ጉታውያን በገቡበት ወቅት አንዳንድ ደቡባዊ ከተማ-አገር እንደ ኡሩክ፣ ኡርና ላጋሽ በራሳቸው ከንቲቦች ሥር ነጻ ሆነው ነበር። ሆኖም የአካድ መንግሥት መጨረሻ ውድቀት በኤላም ንጉሥ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ ዕጅ እንደ ደረሰ ይመስላል።
ቀዳሚው ዱዱ |
የአካድ ንጉሥ 2001-1986 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ የለም |
ተዋቢ መጻሕፍት
Wikiwand in your browser!
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.