From Wikipedia, the free encyclopedia
ሞሪሸስ በሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ በማዳጋስካር አጠገብ የተገኘው ደሴት አገር ነው። ከ፩ ሚሊዮን ኗሪዎች በላይ አሉበት። በ1960 ዓም ነፃነት ከዩናይትድ ኪንግደም አገኘ።
እስከ 1673 ዓም ድረስ ሕልውና የነበረው የታላቅ ወፍ ዝርያ ዶዶ በሞሪሸስ ብቻ ይገኝ ነበር፤ በዚያውም ወቅት መጨረሻው የዶዶ ወፍ አለቀ። የሰው ልጆች ግን እስከ 1500 ዓም ያህል ድረስ አልኖሩበትም። ከዚያ የኔዘርላንድና የፈረንሳይ ሰዎች ይሠፈሩበት ነበር።
ሸንኮራ ኣገዳ የሞሪሸስ ዋነኛ ምርት ነው፤ ከዚህም አረቄ ይሠራል። ኗሪዎቹ አሁን በብዛት ከሕንድ ስለ ሆኑ፣ ከግማሽ በላይ የሂንዱ ሃይማኖት ተከታዮች ናቸው። የተወደዱት እስፖርቶች እግር ኳስና ራግቢ ናቸው።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.