ሐምሌ ፲፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፲፫ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፶፫ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ፤ ማቴዎስ፤ እና ማርቆስ ደግሞ ፶፪ ቀናት ይቀራሉ።
አቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም -የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዓለም ባንክን (The World Bank) እና ዓለም አቀፍ ገንዘባዊ ዕድርን (International Monetary Fund - IMF) የመሠረተውን የብሬቶን ዉድስ (Bretton Woods Agreement) ስምምነት አፀደቀ
- ፲፱፻፵፫ ዓ/ም - የዮርዳኖስ ንጉሥ፣ ቀዳማዊ አብዱላ ኢየሩሳሌም ላይ በሚገኝ መስጊድ ውስጥ የዓርብ ጸሎት ላይ እንዳሉ በአንድ የፍልስጥኤም ተወላጅ እጅ ተገደሉ።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም -አፖሎ 11 የተባለው የጠፈር መንኮራኲር ጨረቃ ላይ ሲያርፍ የሰላሳ ስምንት ዓመቱ ኒል አርምስትሮንግ የጨረቃን ነጠፍ በመርገጥ የመጀመሪያው የሰው ልጅ ሆነ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በቆጵሮስ ደሴት ላይ በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት የአገሪቱ ፕሬዚደንት ሊቀ ጳጳስ ማካሪዮስ ከስልጣን በወረዱ በአምስተኛው ቀን፣ የቱርክ ሠራዊቶች ደሴቷን ወረሩ። እስካሁንም ይቺ ደሴት ለሁለት ተከፍላ የግሪክ ቆጵሮስ እና የቱርክ ቆፕሮስ በመባል የሁለቱ ዘሮች የልዩነት መተዳደሪያ ደሴት ናት።
- ፲፱፻፸፪ ዓ/ም -የተባበሩት መንግሥታት ድርጀት አካል የሆነው የጸጥታ ምክር ቤት አባላት ድርጅቱ ኢየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማነቷን እንዳይቀበሉ በሙሉ ድምጽ ወሰነ።
ልደት
ዕለተ ሞት
፲፱፻፵፫ ዓ/ም የዮርዳኖስ ንጉሥ፣ ቀዳማዊ አብዱላ
ዋቢ ምንጮች
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/July 20
Wikiwand in your browser!
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.