From Wikipedia, the free encyclopedia
ሄርሚኖን (ወይም እርሚኖን፣ ሄርሚዮን) በጥንታዊ ጀርመናውያን ነገዶች መካከል አንዱ ዋና ክፍል ነበር። ስሙ በሮማውያን ታሪክ ጸሐፍት እንደ ታኪቱስና ፕሊኒ ዘንድ ይታወቃል።
ፖምፖኒዩስ ሜላ (35 ዓ.ም.) እንዳለው፣ በባልቲክ ባህር ላይ ኪምብሪና ቴውቶኔስ ሲኖሩ ከነሱ ኋላ ሄርሚዮኔስ ከሁሉ በተራቀው ጌርማኒያ (ጀርመን) ክፍል ተገኙ።
ፕሊኒ (70 ዓ.ም. ግድም) እንደ ጻፈው፣ ጀመናውያን በ5 ንዑስ-ብሔሮች ተከፋፈሉ፤ እነርሱም ዋንዲሊ፣ ኢንግዋዮን፣ ኢስትዋዮን፣ ሄርሚዮን፣ እና ባስተርናይ ናቸው። በሄርሚዮን ነገዶች መካከል ስዌቢ፣ ሄርሙንዱሪ፣ ካቲ፣ እና ኬሩስኪ የተባሉ ጎሣዎች እንደ ኖሩ ይለናል።
ታኪቱስ (90 ዓ.ም.) እንደሚለን፣ በጀርመናውያን «ጥንታዊ ዘፈኖች» መሠረት በጥንት ማኑስ ሶስት ልጆች ነበሩት። እነኚህም 3 ልጆች ሦስት ንዑስ-ብሔሮች ወለዱ፦
በ820 ዓ.ም. ግድም ሂስቶሪያ ብሪቶኑም (የብሪታንያውያን ታሪክ) የሚባል መጽሐፍ ተጽፎ፣ የ«አላኑስ» ልጅ «አርሜኖን» ይባላል፤ አምስት ልጆቹም «ጎጡስ»፣ «ዋላጎጡስ»፣ «ኪቢዱስ»፣ «ቡርጉንዱስ»ና «ሎንጎባርዱስ» ሲሆኑ ከነዚህ ጎታውያን፣ ዋላጎታውያን፣ ጌፒዶች፣ ቡርጉንዳውያንና ሎንጎባርዳውያን እንደ ተወለዱ ይላል።
አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ በ1490 ዓ.ም. ባሳተመው ጽሑፍ ዘንድ፣ ሄርሚዮን ከኢንጋይዎን ዘመን በኋላ በሳርማትያ ነገሠ፣ «በመሣርያዎች ሓይለኛ ሰው» ሲለው ሌላ መረጃ ስለርሱ አይሰጥም።
በ1513 ዓ.ም. ግድም ጀርመናዊው መምህር ዮሐንስ አቬንቲኑስ የጀርመን አገር ዜና መዋዕል አሳተመ። በዚህም ውስጥ እንደሚዘግበው፣ ሄርሚኖን የኢስቴዎን ልጅና ተከታይ ነው። ዋና ከተማው በሄርማንስሃይም (የአሁኑ ሬገንስቡርግ) ሆነ። በ764 ዓ.ም. የፍራንኮች ንጉሥ ካሮሉስ ማግኑስ ያጠፋው የአረመኔ ሐውልት «እርሚንሱል» በአቬንቲኑስ ዘንድ ሄርሚኖን ምኲራብ ያሠራበት ሥፍራ ነበር።
ሄርሚኖን የጦር ሠልፍ ትምህርት በጀርመን አገር አቆመ፣ በየአመቱም ብዙ ሺህ ወንዶች በግዴታ ወታደርነት ተመለመሉ ይለናል። በሄርሚኖን ዘመን አፒስ በግብጽ እንደ ነበር ይጨምራል። ሄርሚኖን ከነገሠ በኋላ ልጁ ማርሱስ በጀርመን ዙፋን ላይ ተከተለው ይላሉ።
ቀዳሚው ኢስታይዎን |
የቱዊስኮኔስ (ጀርመን) ንጉሥ | ተከታይ ማርሱስ |
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.