From Wikipedia, the free encyclopedia
ሁኖርና ማጎር በሀንጋሪ አፈ ታሪክ ዘንድ የሁኖችና የሀንጋራውያን (ማውጃሮች) ቅድማያቶች ናቸው።
በአንዳንድ መጻሕፍት መሠረት (ለምሳሌ የመካከለኛ ዘመን ላቲን ዜና መዋዕል ጌስታ ሁኖሩም ኤት ሁንጋሮሩም)፤ መንታ መሳፍንት ሁኖርና ማጎር የ'ታና' ልጅ 'መንሮት'ና የሚስቱ 'ኤነሕ' ልጆች ነበሩ። ይህ 'መንሮት' 200 አመታት ከማየ አይህ በኋላ በባቢሎን ሥልጣን እንደያዘ ሲባል መታወቂያው ደግሞ የኩሽ ልጅ ናምሩድ መሆኑ ይተረካል። መንታዎቹም በፋርስ አገር ተወልደው በአዞቭ ባሕር አጠገብ ለ5 አመት ሲቆዩ አንድ ቀን ነጭ አጋዘንን በማደን ላይ ሒደው ከአላኖች አለቃ 'ዱር' ሴት ልጆች መካከል ለራሳቸው ሚስቶችን አገኝተው እንደወሰዱ ወደ እስኩቴስም እንደ ሄዱ ይባላል። የሁኖር ተወላጆች ሁኖች፣ የማጎርም ልጆች ማውጃሮች እንደሆኑ ይገለጻል።
ጥቂት ደራስያን ደግሞ 'ታና' ወይም 'ኩሽ' ከሱመራዊው ኪሽ ንጉሥ ኤታና ጋር ተመሳሳይነቱን አጠቁመዋል። ከዚህ በላይ የኩሻን መንግሥት (እስኩቴስ) ቅድማያት 'ኩሽ-ታና' በአፈ ታሪክ አጠቁመዋል።
በመካከለኛው ዘመን መጽሐፍ ክሮኒኮን ፒክቱም መሠረት ግን፣ ይህ 'ማጎር' እንዲያውም ማጎግ ሲሆን፣ እሱና ሁኖር የናምሩድ ልጆች ሳይሆኑ የያፌት ልጆች (በኤነሕ) ናቸው።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.