2 ሓኖ ወይም ሓኖ መርከበኛው ከ488 እስከ 448 ዓክልበ. የቀርታግና ንጉሥ ከመሆኑ በላይ ዝነኛ ተጓዥና መርከበኛ ነበረ።

Thumb
የንጉሥ ሓኖ ጉዞ

ስለ ዘመነ መንግሥታቸው ብዙ መረጃ የለም። ነገር ግን ያለን መረጃ የአፍሪካን ጠረፍ በመርከብ ጉዞ እንደ ዞረ የሚናገር ነው። በ478 ዓክልበ. ግድም ከ60 መርከቦች ጋራ ከጂብራልታር ወሽመጥ ውጭ ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ገባ። በነዚህ መርከቦች 30,000 ሰዎች ሲኖሩ በአሁኑ ሞሮኮ ውስጥ 7 ቅኝ ከተሞች እንደ መሠረቱ ተጻፈ። ከዚያ አልፎ እስከ ጋቦን ድረስ እንደ ተጓዘ ይታስባል። በዚያ በአንድ ደሴት በግሪክ «ጎሪላይ» የተባለ በፍጹም ጠጉራምና አውሬ ጎሣ እንዳገኘ ጻፈ፤ ቆዳዎችንም ይዘው ወደ ቀርጣግና ተመለሱ። እነኚህ ሰዎች ሳይሆኑ ጦጣዎች እንደ ነበሩ ስለሚታመን፣ የጦጣ ወገን ስም «ጎሪላ» ከዚህ ታሪክ የተወሰደ ነው።

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.