1 ሐቱሺሊ
From Wikipedia, the free encyclopedia
1 ሐቱሺሊ ምናልባት 1559-1536 ዓክልበ. አካባቢ ከ1 ላባርና በኋላ በኩሻራና በሐቱሳሽ (በሐቲ) አገር) የገዛ ንጉሥ ነበር።
በ1 ሐቱሺሊ አዋጅ ማዕረጉ «ታባርና» ነው፣ ልጆቹን ላባርናና ሁዚያን ስለ ጭካኔያቸው ከወራሽነት ሽሯቸው 1 ሙርሲሊን ወራሹን ያደርገዋል። አያቱም ሕሽሚ-ሻሩማ እንደ ሆነ ይጠቅሳል። በሌላ ሰነድ የንግሥቱ ስም ካዱሺ ተዘረዘረ።
የሐቱሺሊ ዜና መዋዕል ከዘመኑ ስድስቱን አመታት ይገልጻል። በዚህም ውስጥ የ፩ ላባርና ንግስት ታዋናና ወንድም ልጅ መሆኑን ይጠቅሳል።
- .፦ ሐቱሺሊ ሻናኊታን ከበበ፣ ዙሪያውን አጠፋ፣ ዛልፓን አጠፋ፣ አራት ሠረገሎችና ሌሎች ስጦታዎች ለጣኦታት ሰጠ።
- .፦ ሐቱሺሊ ወደ ሶርያ ገብቶ የያምኻድ ንጉሥ 3 ሃሙራቢ ተገዥ የሆነውን የአላላኽ ገዥ አሚታቁ አሸንፎ አላላኽን አጠፋ። ከዚያ ሐቱሺሊ የኡርሹ ሑራውያንን አሸነፋቸው፣ ያምኻድና ከርከሚሽ ረድኤታቸውን ለኡርሹ ምንም ቢሰጡ።[1]
- ፦ ሐቱሺሊ ወደ ምዕራብ ወደ አርዛዋ አገር ገብቶ ከብትና በግ ወሰደ። ይህ እየሆነ በምሥራቅ ያሉት ክፍሎችና ሑራውያን እንደገና ስለገቡበት ተመልሶ አመጹን በማጠፍ ዘመተ።
- ፦ ሐቱቪሊ ወደ ስሜኑ ተመልሶ ሻናኊታንና የዙሪያውን ከተሞች አጠፋቸው።
- ፦ ሐቱሺሊ ወደ ሶርያ ተመልሶ ያምሓድንና ኢሱዋን በደብረ አታሉር ውግያ አሸነፈ፣[2] ኤፍራጥስ ወንዝን ተሻግሮ ኢሡዋንና ሌሎችንም የሖርያውያን ከተሞች አጠፋቸው፣ ብዙ ብርን ዘርፎ ወደ ሐቱሳሽ ላከ።
በ1300 ዓክልበ. በኬጥያውያን ንጉሥ 2 ሙዋታሊ ከዊሉሳ ንጉሥ አላክሳንዱ ጋራ በተዋዋለ ስምምነት እንደሚተርክ፣ የቀድሞ ንጉሥ «ላባርና» አርዛዋንም ዊሉሳንም እንደ ያዘ ሲል ምናልባት 1 ሐቱሺሊ («2 ላባርና») ማለቱ ይሆናል። ሐቱቪሊ ሐለብን ከያምኻድ ግን መቸም አልያዘምና ምናልባት በሐለብ ዘመቻ እያለ ተቆስሎ ሞተ። ይህ ተከታዩ ሙርሲሊ «የአባቴን ደም ቂም በማብቀል» ያምኻድን እንዳጠፋ ስለ ዘገበ ነው።[3][4]
ቀዳሚው 1 ላባርና |
የሐቲ ንጉሥ 1559-1536 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ 1 ሙርሲሊ |
- William J. Hamblin (2006). Warfare in the Ancient Near East to 1600 BC. p. 289. ISBN 9781134520626. http://books.google.nl/books?id=biyDDd0uKGMC&pg=PT289&dq#v=onepage&q&f=false.
- Trevor Bryce (1999). The Kingdom of the Hittites. p. 83. ISBN 9780199240104. http://books.google.nl/books?id=Agg5-lpVI2MC&pg=PA83&dq=#v=onepage&q&f=false.
- Charles Burney (2004). Historical Dictionary of the Hittites. p. 107. ISBN 9780810865648. http://books.google.nl/books?id=azPl5Jzv930C&pg=PA107#v=onepage&q&f=false.
Wikiwand in your browser!
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.