From Wikipedia, the free encyclopedia
ፕሩሲያ ከ1517 እስከ 1939 ዓም ድረስ የጀርመን ድሮ ክፍላገር ነበር።
ከዚያ በፊት ጥንታዊ ፕሩሲያ ከ500 ዓም ያህል (በትውፊት ዘንድ) ጀምሮ እስከ 1216 ዓም ድረስ የተገኘ አረመኔ አገር ሆኖ ነበር። ቋንቋቸው ጥንታዊ ፕሩስኛ የባልቲክ ቋንቋዎች አባል ነበር። ከ1216 እስከ 1275 ዓም ያህል ድረስ፣ ቴውቶኒክ ሥርዓት የተባለው የመስቀለኞች ሥራዊት በጦርነት አሸነፋቸው፣ በክርስትና እንዲጠመቁ አስገደዳቸውና መሬታቸውን ያዙ። አገሩ እስከ 1517 ዓም ድረስ ቴውቶኒክ ግዛት ተባለ።
በ1517 ዓም በፕሮቴስታንት ተሃድሶ ንቅናቄ ዘመን፣ የቴውቶኒክ ግዛት አለቃ አልቤርት ዘፕሩሲያ የፕሮቴስታንት ሉተራን ቤተ ክርስቲያን ምዕመን ሆነና ከሮሜ ፓፓ ነጻነት ስለ አዋጀ፣ ግዛቱ ያንጊዜ የፕሩሲያ መስፍንነት ተባለ። ይህ በ«ቅዱስ ሮማዊ መንግሥት» (ጀርመን) ውስጥ ክፍላገር ነበረ። ፕሮቴስታንቶች ከብዙ አገራት በስደት ወደ ፕሩሲያ ፈለሱ፤ የክፍላገሩም ዋና ቋንቋ ጀርመንኛ ነበር። ጥንታዊ ፕሩስኛ ቀስ በቀስ እየጠፋ ከ1700 ዓም በኋላ በሙሉ ተረሳ።
የፕሩሲያ ጀርመናዊ አለቆች ደግሞ ግዛታቸውን በጀርመን ውስጥ እጅግ ለማስፋፋት ስለ ቻሉ፣ ከ«ቅዱስ ሮማዊ መንግሥት» ዘመን ቀጥሎ ጀርመን እንደ ዘመናዊ መንግሥት በማዋኸድ አንጋፋ ሚና ያለው ክፍላገር ሆነ።
በናዚ ጀርመን አዶልፍ ሂትለር በ1925 ዓም ወደ ሥላን ሲመጣ የክፍላገሩን ነጻ መንግሥት አጠፋ፤ ሆኖም በይፋ እንደ ክፍላገር እስከ 1939 ዓም ቆየ፤ በ1939 ዓም በጦር ጓደኞቹ አዋጅ ፕሩሲያ በይፋ ተጨረሰ።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.