From Wikipedia, the free encyclopedia
ፒያኖ በቁልፎች ድርድር ለመጫወት የሚያስችል ዘመናዊ የሙዚቃ መሳሪያ ነው። ይህ መሣሪያ በአለማችን ላይ እጅግ የተለመደ ሲሆን በተለይም በሙዚቃ መሣሪያ ብቻ ለተቀናበሩ ሙዚቃዎች መስሪያነት ያገለግላል። በቀላሉ ለመያዝ የማይመች እና ዋጋውም እጅግ በጣም ውድ በመሆኑ በቀላል የሙዚቃ ቡድኖች ውስጥ አይገኝም። በዚህም ለከፍተኛ የሙዚቃ ቅንብሮች እና ትዕይንቶች ዋናውን ሚና የሚጫወት መሣሪያ ነው። በፒያኖ ላይ አንድን ቁልፍ መጫን ከበስተኋላው ያለው ወካይ መዶሻ ከብረት ተሠርተው የተወጠሩትን ጅማቶች እንዲመታ እና ድምፅ እንዲፈጥር ያደርገዋል።
የመጀመሪያው ዘመናዊ ፒያኖ የተሠራው ጣልያን ሀገር ውስጥ በባርቶሎሚዮ ክሪስቶፎሪ (1655 –1731) ሲሆን ይህ ሠው በፈርዲናንዶ ዲ መዲቺ የሙዚቃ መሣሪያ ጠባቂ ተደርጎ የተቀጠረ ሠው ነበር።
እንደ ሃይድን፣ ሞዛርት እና ቤትሆቨን የሉ የሙዚቃ ጠበብቶች የተጠቀሙበት ፒያኖ በአሁኑ ጊዜ ካለው ፒያኖ እንደሚለይ ግልፅ ነው። የሮማንቲኮች ሙዚቃ ለራሱ የተፃፈው ከዘመናዊዮቹ ፒያኖዎች የተለየ ተደርጎ ነው።
ዘመናዊዩ ፒያኖ በሁለት ዓይነት ተመርቶ ይቀርባል። እነዚህም ግራንድ ፒያኖ እና አፕራይት ፒያኖ ናቸው።
ማለት
ጂ፡ቁልፍ
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.