![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/2/28/Kelp_In_Freycinet_Tasmania.jpg/640px-Kelp_In_Freycinet_Tasmania.jpg&w=640&q=50)
ፋይኮሎጂ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ፋይኮሎጂ የሚለው ቃል «የባህር አረም» የሚል ትርጓሜ ካለው (φῦκος) /ፉኮስ/ ከተሰኘ የጥንታዊ ግሪክ ቃል እና «ጥናት» የሚል ትርጓሜ ካለው (-λογία) /ሎጊያ/ ከተሰኘ የግሪክ ቃል ጥምረት የመጣ ሲሆን የዋቅላሚዎች ሳይንሳዊ ጥናት ማለት ነው። አልጎሎጂ በመባልም ይታወቅ የነበር ሲሆን ፋይኮሎጂ የሥነ-ሕይወት ዘርፍ ነው።
![ከልፕ](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/2/28/Kelp_In_Freycinet_Tasmania.jpg/640px-Kelp_In_Freycinet_Tasmania.jpg)
ዋቅላሚዎች በውሃ ስነ ምህዳር ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ ምርት በመሆን ያገለግላሉ። አብዛኛዎቹ ዋቅላሚዎች ውን ኑክለሳውያን, የብርሃን አስተጻምሮ የሚያካሂዱ እና እርጥበት ባለበት አካባቢ የሚኖሩ ፍጥረታት ናቸወ። ከከፍተኛ ተክሎች የሚለዩት በእውነተኛ ሥሮች፣ ግንዶች ወይም ቅጠሎች የሌላቸው በመሆኑ ነው። አበቦችን አያብቡም። ብዙ ዝርያዎች ነጠላ-ሕዋስ እና ጥቃቅን (ፋይቶፕላንክተን እና ሌሎች ደቂቅ ዋቅላሚዎችን ጨምሮ) ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ በአንድ ወይም በሌላ ደረጃ ባለብዙ ህዋሳት ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹእንደ ከልፕ እና ሳርጋሰም ያሉ የባህር አረሞች ወደ ትልቅ መጠን ያድጋሉ ።
ፋይኮሎጂ ሰማያዊ አረንጓዴአማ ዋቅላሚዎች ወይም ሲያኖባክቴርያ በመባል የሚታወቁትን ቅድመ ኑክለሳውያን ጥናትያካትታል።በርከት ያሉ ጥቃቅን ዋቅላሚዎች እንዲሁ በላይከን ውስጥ እንደ ተደጋጋፊ አካላት በመሆን ይገኛሉ።
ፋይኮሎጂስቶች በአብዛኛው የሚያተኩሩት በለጋውሃ ወይም በውቅያኖስ ዋቅላሚዎች ላይ ሲሆን፣ በተጨማሪ ከእነዚህ ዘርፎች ውስጥ ደግሞ በባልጩት ዋቅላሚዎች ወይም ለስላሳ አካል ባላቸው ዋቅላሚዎች ላይ ሊሰሩ ይችላሉ።