ፋሲል ግቢ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ፋሲል ግቢ ወይንም ነገሥታት ግቢ በጎንደር ከተማ የሚገኝ የቤተመንግስታት ግምቦች ስብስብ ነው። ግቢው የተመሰረተው በ1628ዓ.ም. በዓፄ ፋሲለደስ ነበር። ማቀባበያ የሚሰኘው የግቢው አጥር 900ሜትር ርዝመት[1] ሲኖረው በውስጡ 70፣000 ስኩየር ሜትር የመሬት ይዞታ ያካልላል። አጼ ፋሲለደስ የመጀመሪያውንና ታላቁን ግንብ ያሰሩ እንጂ፣ ከርሳቸው በኋላ የተነሱት ነገሥታትም ለ220 ዓመታት የየራሳቸውን ህንጻ በመስራት ቦታው በቅርስ እንዲዳብር አድርገዋል። በግቢው የመጨረሻውን ህንጻ ያሰራችው ንግሥት ብርሃን ሞገስ ነበርች።
Quick Facts የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ቅርስ, ፋሲል ግቢ ...
| ||||
---|---|---|---|---|
ፋሲል ግቢ | ||||
ፊት ለፊት ፋሲል ግምብ፣ በግራ ቀዳማዊ ዮሐንስ ጽሕፈት ቤት | ||||
አገር | ኢትዮጵያ | |||
ዓይነት | ባሕላዊ | |||
መመዘኛ | c(ii)(iii) | |||
የውጭ ማጣቀሻ | 19 | |||
አካባቢ** | አፍሪካ | |||
የቅርስነት ታሪክ | ||||
ቅርስ የሆነበት ጊዜ | 1971 (3ኛ ጉባኤ) | |||
* በዩ.ኔ.ስ.ኮ ስሙ እንደሰፈረ። ** የዩ.ኔ.ስ.ኮ. ክልል ክፍፍል |
Close
ግቢው ገናና በነበረበት ዘመን በሽወች የሚቆጠሩ ቤቶችና ሱቆችን በውስጡ ያቅፍ ነበር። በጥንቱ ዘመን የአስተዳደር ስርዓት ተቀርጾለት በጥንቃቄ የሚመራ ነበር። ስርዓቱም ስርዓተ መንግስት በመባል ሲታወቅ በመጽሃፍ መልኩ በግዕዝና በድሮው አማርኛ የተመዘገበ ነበር።
የሚከተለው ካርታ ላይ ማውስወን ቢያንሳፍፉ፣ እያንዳንዱ የግቢው ህንጻና በሮች ስም ወጥቶ ይታየወታል፡፡ ሲጫኑም ወደዚያ ክፍል ማብራሪያ ይወስደወታል።[2] | |