![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/1/1e/Venn1011.svg/langam-640px-Venn1011.svg.png&w=640&q=50)
ጥገኛ አምክንዮ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ጥገኛ አምክንዮ በሁለት የአምክንዮ ዋጋወች የሚተገበር ሲሆን፣ ውጤቱ ውሸት የሚሆነው ቀዳሚ አረፍተ ነገሩ እውነት ሁኖ ተከታይ አረፍተ ነገሩ (ጥገኛ አረፍተ ነገሩ) ውሸት ሲሆን ብቻና ብቻ ነው። (ቀዳሚና ተከታይ አረፍተ ነገር ምን ማለት እንደሆነ ከታች ሙሉ ማብራሪያ የሚለውን ክፍል ይመልከቱ ) ከአምክንዮ አንጻር ጥገኛ አምክንዮ ከአይደለም....ወይም... ጋር እኩል ነው። በሂሳብ አጻጻፍ፣ p ቀዳሚ አረፍተ ነገር (አስጠጊ) ቢሆንና q ተከታይ (ጥገኛ) ቢሆን፣ የጥገኝነት ዝምድናቸው እንዲህ ይጻፋል p → q ፡ ሲነበብ p ስለዚህ q ነው። ይህ እንግዲህ ከላይ እንደተጠቀሰው ከ አይደለም p ወይም q ጋር ምንም ለውጥ የለውም። ይህን የመጨረሻውን ግኝት
![](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/1/1e/Venn1011.svg/320px-Venn1011.svg.png)
ጥገኝነት በሂሳብ ትርጓሜው እንዲህ ይሰፍራል
![](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/1/1e/Venn1011.svg/40px-Venn1011.svg.png)
![](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/e/eb/Venn1010.svg/40px-Venn1010.svg.png)
![](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/7/76/Venn0011.svg/40px-Venn0011.svg.png)
በምሳሌ እንይ፡
- መሰረት አዲስ አበባ ውስጥ ናት፣ ስለዚህ መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ ናት
ከላይ በጻፍነው ትርጓሜ አንጻር ሲተረጎም
- መሰረት አዲስ አበባ ውስጥ አይደለችም ወይም መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ ናት
ከላይ የተጻፉትን አረፍተ ነገሮች አነጻጽረው እኩለነታቸውን ያረጋግጡ
More information * ትርጓሚያዊ እኩለንት:
...
የጥገኛ አምክንዮ ጸባዮች | ትርጓሜ ከእውነታ ሰንጠረዥ አንጻር | ||
---|---|---|---|
* ትርጓሚያዊ እኩለንት: | p | q | p ⇒ q |
*ጥገኝነት የራሱ ነጸብራቅ ነው: | እውነት | እውነት | እውነት |
*ጥገኝነት ተሻጋሪ ነው: | እውነት | ውሸት | ውሸት |
*ጥገኝነት ታዳይ ነው: | ውሸት | እውነት | እውነት |
ውሸት | ውሸት | እውነት |
Close